የክልሉ መንግሥት የበጀት ዓመቱን የመጀመሪያ ግማሽ ዓመት ዕቅድ አፈጻጸም ከመገምገም ባሻገር ቀጣይ ትኩረት በሚሹ ጉዳዮች ላይ በመወያየት አቅጣጫ አስቀምጧል።የመንግሥት ኮሙኒኬሽን ጉዳች ቢሮ
የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልላዊ መንግሥት የመንግሥት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ የክልሉ መንግሥት የ2017 በጀት ዓመት 1ኛው ግማሽ ዓመት የዕቅድ አፈጻጸምና የቀጣይ ትኩረት አቅጣጫ አድርጎ ያስቀመጣቸው ጉዳዮችን አስመልክቶ ለጋዜጠኞች መግለጫ ሰጥቷል። የክልሉ መንግሥት የ2017 በጀት ዓመት 1ኛው ግማሽ ወራት ዕቅድ አፈጻጸም የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ኢንጂነር ነጋሽ ዋጌሾ (ዶ/ር)፣የክልሉ ብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ፍቅሬ አማንን…
