Trendings

በሚዛን አማን ከተማ በአራት ቀበሌዎች 1 ሺህ 148 ይዞታዎች ወደ ህጋዊ ትግበራ መግባታቸው ተገለጸ ።

በሚዛን አማን ከተማ አስተዳደር እየተከናወኑ የሚገኙ የሴፍትኔት ፕሮግራሞች እና የማዘጋጃ ቤታዊ አገልግሎቶች ዙሪያ ምልከታ ተደርጓል ። የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን ቢሮ ኃላፊ ኢንጂነር የማታለም ቸኮል በከተማ አስተዳደር ተገኝተው ምልከታ አድርገዋል። በምልከታው ወቅት የከተማው ማዘጋጃ ቤት ዋና ስራ አስኪያጅ አቶ አሰፋ ቤሪ እንደገለጹት በክልሉ ደንብና መመሪያ ወጥቶ በስራ ላይ የሚገኘው ሳይፈቀዱ የተያዙ…

Read More

ተቋርጦ የነበረውን የቴፒ አይሮፕላን ማረፊያ መልሶ ወደ ስራ ለማስገባት በሚያስችሉ ጉዳዮች ላይ ከማሻ ከተማ ነጋዴዎችና የግል ባለሀብቶች ጋር የውይይት መድረክ ተካሄደ።

የማሻ ወረዳና የከተማ ነዋሪዎች በበኩላቸው ለእቅዱ እውን መሆን የበኩላቸውን እንደሚወጡ ተናግረዋል። በመድረኩ ላይ የተገኙት የሸካ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ አበበ ማሞ ዞኑ እምቅ የተፈጥሮ ሀብት ባለቤት ብቻ ሳይሆን ሰፊ የመልማት እድል ያለው ከመሆኑ ጋር ተያይዞ መሰል የትራንስፖርት አገልግሎት ማስፈለጉን ተናግረዋል። ከዚህ ቀደም ምንም ስልጣኔ ባልተስፋፋበት ወቅት የቴፒ አየር ማረፊያ ከ1950 ዓመተ ምህረት ጀምሮ አገልግሎት እየሰጠ…

Read More

የፌደራል መንግስት ድጋፋዊ ሱፐርቪዥን ቡድን በክልሉ ያካሄደውን የጉብኝት ማጠቃለያ ውይይት መድረክ ዛሬ በቦንጋ ከተማ ከክልሉ፣ከዞን ከፍተኛ አመራሮች ጋር አካሂዷል፡፡

የፕላንና ልማት ሚኒስቴር ሚኒስትር እና የሱፐርቪዥን ቡድኑ ሰብሳቢ ዶ/ር ፍጹም አሰፋ ከሠላምና ፀጥታ አንፃር ክልሉ ሠላም መፈጠሩን እና አጎራባች ክልል እና ህብረተሰቡ ጋር የሠላምና ፀጥታ ትብብር መኖሩ የሚበረታታ እንደሆነ ገልጸዋል፡፡ በክልሉ በሠላምና ፀጥታ ዘርፍ የተገኙ ውጤቶች ለማስቀጠል የማህበረሰብ ተኮር የሰላም ግንባታ በማጠናከር የአከባቢ ሠላምና ፀጥታ ጠባቂ እና ባለቤት የማድረግ ስራ እንዲጠናከር አስተያየት ሰጥተዋል። በክልሉ አረንጓዴ…

Read More

እንደ ክልል ትልቁ ሀብታችን ለሆነው የእንስሳት ሀብት ልማት ዘርፉ ልዩ ትኩረት ያስፈልጋል ፦ አቶ ታመነ በቀለ::

ሚዛን አማን ፣ መጋቢት 14/2016 በክልሉ ግብርና ቢሮ ለእንስሳት ጤና ባለሙያዎች ሲሰጥ የቆየው የአቅም ግንባታ ስልጠና ተጠናቋል። በኢትዮጵያ ከሀገራዊ ጥቅል ምርት የግብርና ዘርፉ 65 በመቶ ያህሉን የሚይዝ ሲሆን ከዚህ ውስጥ 48 በመቶ የሚጠጋው ደግሞ ከእንስሳት ሀብት ልማት የሚሸፈን መሆኑን ጥናቶች ያመላክታሉ። በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልልም እንደ ክልል አሉ ከሚባሉ ሀብቶች ቀዳሚው የእንስሳት ሀብት ልማቱ…

Read More

ከመጋቢት አጋማሽ ጀምሮ እስከ ግንቦት መጨረሻ ድረስ ከባድ የበልግ ዝናብ ልኖር ስለሚችል ህብረተሰቡ አስፈላጊውን ጥንቃቄ እንዲያደርግ የክልሉ አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን አሳሰበ::

በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ደጋማ አከባቢዎች ከመጋቢት አጋማሽ ጀምሮ እስከ ግንቦት መጨረሻ ድረስ ከባድ የበልግ ዝናብ ልኖር ስለሚችል ህብረተሰቡ አስፈላጊውን ጥንቃቄ እንዲያደርግ የክልሉ አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን ኮሚሽነር ዶ/ር ለማ መሠለ አሳስበዋል። የብሔራዊ ሜትሮዎሎጂ መረጃን ዋብ ያደረጉ ዶ/ር ለማ በክልሉ በተለይ በደጋማ አከባቢዎች በሚኖረው ከባድ የበልግ ዝናብ ጎርፍና ናዳ ልኖር እንደሚችልም አስረድተዋል። በተለይ…

Read More

ከተሞች ያላቸው መሠረታዊ ሀብት መሬት ነው።

ውስንና ውድ የሆነውን የከተማ መሬት በአግባቡ መለየት፣በፕላን መምራትና ማስመዝገብ ካልተቻለ ከተሞች ሀብት የማመንጨት ውስንነት፣አስፈላጊ መሠረተ ልማቶችን ያለማሟላት፣ የመልማት ችግርና ለህገወጥነትና ለተለያዩ ብልሹ አስራሮች ተጋላጭ ይሆናሉ። የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልላዊ መንግስት ከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን ቢሮ ክልሉ ከተመሠረተ ጊዜ ጀምሮ የከተማ መሬት አስተዳደር ጋር በተያያዘ የይዞታና ምዝገባ፣ማዘጋጃ ቤታዊ አገልግሎቶችን ማዘመንና የመሬት አቅርቦትና ስርጭትን ከማሳለጥ አኳያ ሰፊ…

Read More

የቦንጋ ዩኒቨርሲቲ ከሁለት የሩሲያ ተቋማት ጋር የሶስትዮሽ የመግባቢያ ስምምነት ተፈራረመ

የቦንጋ ዩኒቨርሲቲ Delivery and Distribution of Paramedic-Midwifery Stations በአገራችን ለመገንባት የሚያስችል የመግባቢያ ስምምነት Herroes Foundation እና Pan African Public Private Partinership Development Center ከተባሉ ሁለት የሩሲያ ተቋማት ጋር በጋራ ለመስራት የሚያስችላቸውን የሶስትዮሽ የመግባቢያ ስምምነት እ.ኤ.አ. ማርች 20 ቀን 2024 በኤምባሲው ጽ/ቤት ተፈራርመዋል፡፡ የሚሲዮኑ መሪ ክቡር አምባሳደር ቻም ኡጋላ በፊርማ ስነ-ስርዓቱ ወቅት ባደረጉት ንግግር በዛሬው እለት…

Read More

ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ ከደቡብ ሱዳን ፕሬዚዳንት የሀገሪቱ ታላቁ የኒሻን ሽልማት ተበረከተላቸው

የኢፌዴሪ ጦር ሀይሎች ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ ከደቡብ ሱዳን ሪፐብሊክ ፕሬዚዳንትና የጦር ሃይሎች ዋና አዛዥ ሳልቫ ኪር ማያርዲት የሀገሪቱ ታላቁ የኒሻን ሽልማት ተበርክቶላቸዋል፡፡ ሽልማቱ የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት ለደቡብ ሱዳን ህዝብ ነፃነትና ሉአላዊነት መከበር ለከፈለው ታላቅ መስዋዕትነትና ላደረገው ድጋፍ መሆኑ ተገልጿል፡፡ ፕሬዚዳንት ሳልቫ ኪር በወቅቱ÷ ኢትዮጵያ በቸገረን ጊዜ ሁሉ መጠጊያችን እና መጠለያችን ከመሆኗም…

Read More

ብልጽግና ፓርቲ በሁለት አመት ከግማሽ በሁሉም ዘርፎች ያከናወናቸው ተግባራት በማስቀጠል የነበሩ ጉድለቶችን በማረም አባሉና አመራሩ በቀጣይ ይበልጥ በቁርጠኝነት ሊሰራ ይገባል ተባለ

በሸካ ዞን በሁሉም ከተማና ወረዳ አስተዳደሮች ሲደረገ የነበረው የብልጽግና ፓርቲ አባላት ዞናዊ የማጠቃለያ ኮንፈረንስ ተጠናቋል። “ቃልን በተግባር ለኢትዮጵያ ብልፅግና” በሚል መሪ ቃል ፓርቲው በግማሽ የምርጫ ዘመን ያከናወናቸውን ተግባራት በማጠናከር ጉድለቶችን በማረም በቀጣይ ጊዜያት አባላቱና አመራሩ ሚናቸውን በተገቢው እንዲወጡ ተጠይቋል። የሸካ ዞን ብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ አለማየሁ አለሙ በመድረኩ እንደገለጹት ፓርቲው በምርጫ ወቅት ለህዝብ…

Read More

ብልጽግና ፓርቲ በሀገራዊ ምርጫ ለህዝቡ የገባውን ቃል በተግባር እየፈጸመ ያለ ፓርቲ መሆኑ ተገለፀ::

በምዕራብ ኦሞ ዞን “ቃል በተግባር ለኢትዮጵያ ብልጽግና” በሚል መሪ ቃል ዞን አቀፍ የብልፅግና ፓርቲ የአባላት የማጠቃለያ ኮንፈረንስ ተጠናቋል። የዞኑ ብልፅግና ፓርቲ ቅርንጫ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ በድሉ መዓዛ እንደተናገሩት ፓርቲያችን በሁለት ዓመት ተኩል ጉዞ ውስጥ የፓርቲ እሳቤ፣ አደረጃጀት እና አባትን አስተሳስሮ በመምራት “ቃል በተግባር” የሚለውን አስተሳሰብ ወደ ውጤት የቀየረ ነው ብለዋል ። ኮንፍራንሱ ባለፉት ሁለት ዓመት…

Read More