በክልሉ የሚሰበሰበው ገቢ ውጤታማ ለማድረግ በቴክኖሎጂ የተደገፈ የአገልግሎት አሰጣጥ ስርዓትን ማጠናከር ይገባል ስሉ ዶክተር ኢንጂነር ነጋሽ ዋጌሾ ገለጹ
የክልሉ ገቢዎች ቢሮ የ2017 በጀት ዓመት የ10 ወራት የገቢ አሰባሰብ የምክክር መድረክ ከባለድርሻ አካላት ጋር አድርጓል ። በምክክር መድረኩ የተገኙት የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ርዕሰ መስተዳድር ዶክተር ኢንጂነር ነጋሽ ዋጌሾ ክልሉ የሚያመነጨውን ገቢ አሟጦ ገቢን በመሰብሰብ ህብረተሰቡ የሚጠይቀውን የልማት ጥያቄ መመለስ ይገባል ብለዋል። በክልሉ የግብር ስወራንና የገቢ ማጭበርበርን ለመከላከል በቴክኖሎጂ የተደገፈ የአገልግሎት አሰጣጥ ስርዓትን…
