በሎስ አንጀለስ ሰነድ አልባ ነዋሪዎችን ማሰር በመጀመሩ የተነሳውን ተቃውሞ ተከትሎ ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ ብሔራዊ ዘባቸውን ወደ አካባቢው አዘመቱ
ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ 2ሺህ የብሔራዊ ዘብ ጠባቂዎችን ወደ ሎስ አንጀለስ አሰማርተዋል። ፕሬዚዳንቱ ይህን ያደረጉት ሰነድ አልባ ነዋሪዎችን የማሰር ዘመቻን ተከትሎ ለተነሳው ተቃውሞ ምላሽ ነው። የአካባቢው ባለስልጣናት ተቃውሞውን መቋቋም ተስኗቸዋል ያሉት ፕሬዚዳንት ትራምፕ፥ የፌደራል መንግስት ችግሩን መፍታት ባለበት መንገድ ይፈታልም ብለዋል። የካሊፎርኒያ ስቴት ገዥ የሆኑት ጋቪን ኒውሶም የትራምፕ ርምጃ ውጥረቶችን እንደሚያባብስ ተናግረዋል። “ይህ የተሳሳተ ተልእኮ ነው…
