በሚቀጥሉት አሥር ቀናት በተለይም በምዕራብ አጋማሽ የሀገሪቱ ክፍሎች የተሻለ ርጥበት ይኖራቸዋል – ኢንስቲትዩቱ
በሚቀጥሉት አሥር ቀናት በተለይም በምዕራብ አጋማሽ የሀገሪቱ ክፍሎች የተሻለ የርጥበት ሁኔታ እንደሚኖራቸው የኢትዮጵያ ሚቲዎሮሎጂ ኢንስቲትዩት አስታወቀ። ኢንስቲትዩቱ በሚቀጥሉት አስር ቀናት የሚኖረውን የአየር ትንበያ አስመልክቶ ለኢዜአ በላከው መግለጫ በሚቀጥሉት ቀናት የሚኖረው የአየር ሁኔታ ለእርሻ ስራ እንቅስቃሴ በአመዛኙ አዎንታዊ ሚና እንደሚኖረው አመላክቷል። ከዚህም ጋር ተያይዞ በምዕራብ እና በሰሜን ምዕራብ የሀገሪቱ አካባቢዎች የሚጠበቀው ከባድ ዝናብ ለወቅቱ የእርሻ ስራ…
