Trendings

በቅርብ ዓመታት ውስጥ፣ ዲጂታል ማንነት ተስፋ ሰጪ ከሆነው ፈጠራ ወደ ዲጂታል ትራንስፎርሜሽን መሠረታዊ ምሦሶ ተሻሽሏል። ከአሁን በኋላ አማራጭ ሳይሆን ሰዎችን ከአገልግሎቶች፣ ከማኅበረሰቦች፣ ከተቋማት እና ከመንግሥታት ጋር የሚያገናኝ አስፈላጊ መሠረተ ልማት ነው።

ከአምስት ዓመት በፊት በዲጂታል ኢትዮጵያ 2025 ራዕይ እየተመራን እጅግ አስፈላጊ ውሳኔ ወስነናል። ይህም ዘመናዊ፣ አካታች፣ መሠረት ያለው እና ሊሰፋ የሚችል ዲጂታል የማንነት ሥርዓት መገንባት ነው። ይሄንንም ለእያንዳንዱ ነዋሪ ተደራሽ እንዲሆን ማድረግ ነበር። ይሄንን ሥርዓት ‘ፋይዳ’ ብለን እንጠራዋለን። ፋይዳ ካርድ ብቻ አይደለም። የግለሰቦችን ግላዊ መረጃዎች ምሥጢራዊነት በመጠበቅ እና አስፈላጊ የሆነውን ብቻ በማጋራት ማንነትዎን የሚያረጋግጥ ልዩ መለያ…

Read More

ጉባኤው በአፍሪካ ጉዳዮች ላይ የጋራ ድምጽ ማሰማት የሚቻልበትን ዕድል ማመቻቸት ነው

የአፍሪካ ማኅበራዊ ሚዲያ ተፅዕኖ ፈጣሪዎች ጉባዔ (ASMIS) ዋነኛ ዓላማም በተፅዕኖ ፈጣሪዎች መካከል ጠንካራ ትብብር በመፍጠር በአፍሪካ ጉዳዮች ላይ የጋራ ድምጽ ማሰማት የሚችሉበትን ዕድል ማመቻቸት እንደሆነ የፐልስ ኦፍ አፍሪካ አስተባባሪ አቶ በረከት ሲሳይ ገለጹ። የአፍሪካውያንን አጀንዳ ለማስረፅና የጋራ ድምፅን ለማሰማት ዕድል የሚፈጥር መሆኑንም አክለዋል። ፐልስ ኦፍ አፍሪካ (Pulse of Africa-POA) ከ ኤ.ጂ.ኤ የቴክኖሎጂ ኢንተርፕራይዝ (AGA-Tech) ጋር…

Read More

የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና መሰጠት ጀመረ

የ2016 ዓ.ም ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት መልቀቂያ የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና መሰጠት ጀምሯል። በዛሬው ዕለት የ12ኛ ክፍል የማህበራዊ ሳይንስ ተፈታኝ ተማሪዎች በዩኒቨርሲቲዎች ፈተናቸውን እየወሰዱ መሆኑ ታውቋል፡፡ ፈተናውን በይፋ ያስጀመሩት የትምህርት ሚኒስትሩ ብርሃኑ ነጋ (ፕ/ር)÷ ዛሬ የሚሰጠው ፈተና ለመጀመሪያ ጊዜ የበይነ መረብና የወረቀት ፈተና በድብልቅ ነው ብለዋል። በመላ ሀገሪቱ የተጀመረው የበይነ መረብና የወረቀት ፈተና እንደ ሀገር…

Read More

የኢትዮጵያ የባሕር በር ባለቤትነት ጥያቄ ተገቢና ለሀገሪቱ የኢኮኖሚ ዕድገት ወሳኝ ነው

የኢትዮጵያ የባሕር በር ባለቤትነት ጥያቄ ተገቢና ለሀገሪቱ የኢኮኖሚ ዕድገት ወሳኝ መሆኑን በኢትዮጵያ የኖርዌይ እና የባንግላዲሽ አምባሳደሮች ገለጹ። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) በቅርቡ ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ማብራሪያ በሰጡበት ወቅት ኢትዮጵያና ቀይ ባሕር በሕግ፣ በመልክዓምድር፣ በታሪክና ሌሎች መለኪያዎች ሊነጣጠሉ እንደማይችሉ ገልጸዋል። በኢትዮጵያ የኖርዌይ አምባሳደር ስቲያን ክሪስቴንሰን እና በኢትዮጵያ የባንግላዲሽ አምባሳደር ኤር ቫይስ ማርሻል ሲትዋት ናይም ለኢዜአ…

Read More

48ኛው የአፍሪካ ሕብረት የሥራ አስፈጻሚ ምክር ቤት መደበኛ ስብሰባ መካሄድ ጀመረ

48ኛው የአፍሪካ ሕብረት የሥራ አስፈጻሚ ምክር ቤት መደበኛ ስብሰባ በአዲስ አበባ መካሄድ ጀምሯል። በስብሰባው የመክፈቻ ሥነ-ሥርዓት ላይ የአፍሪካ ሕብረት ኮሚሽን ሊቀመንበር መሐመድ አሊ ዩሱፍ፣ የኢፌዴሪ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጌዲዮን ጢሞቴዎስን (ዶ/ር) ጨምሮ የሕብረቱ አባል ሀገራት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች፣ ከፍተኛ ዲፕሎማቶች፣ የሕብረቱ ተቋማት አመራሮችና ሌሎች ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል። የሥራ አስፈጻሚ ምክር ቤቱ ዛሬና ነገ ለሁለት…

Read More

“የፊቼ ጫምባላላ የዘመን መለወጫ በዓል ከሀገር ሀብቶችና ቅርሶች መካከል አንዱ ነው”፦ የመንግሥት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት

የፊቼ ጫምባላላ የዘመን መለወጫ በዓል ከሀገር ሀብቶችና ቅርሶች መካከል አንዱ ነው ሲል የመንግሥት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ገለጸ። አገልግሎቱ የፊቼ ጫምባላላ የዘመን መለወጫ በዓልን ምክንያት በማድረግ ያስተላለፈው የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት እንደሚከተለው ቀርቧል፦ እንኳን ለፊቼ ጫምባላላ የዘመን መለወጫ በዓል በሰላም አደረሳችሁ! ከተባበሩት መንግሥታት የትምህርት፣ የሳይንስና የባህል ድርጅት (ዩኔስኮ) የማይዳሰሱ ቅርሶች መካከል ተመዝግቦ የሚገኘው የፊቼ ጫምባላላ የዘመን መለወጫ በዓል…

Read More

የሀገራዊ ምክክሩ ኮሚሽን የአጀንዳ ቀረጻና የምክክር አስተባባሪ አቶ ተመስገን አብዲሳ አጀንዳና ተያያዥ ጉዳዮች ላይ ማብራሪያ ሰጥተዋል ።

አቶ ተመስገን አብዲሳ ለኮሚሽኑ በአጀንዳነት የሚቀርቡ አጀንዳዎች አጀንዳ የሚያስብላቸው መገለጫ ባህሪያቸው፣ የአጀንዳዎቹ መዳረሻቸው የት እንደሆነ፣ የአጀንዳ ባህሪያትስ ምንድናቸው? የኮሚሽኑ የአጀንዳነት መስፈርት ምን ምንድ ናቸው ? በሚሉ ርዕሰ ጉዳዮች ላይ ለሚዲያ ማብራሪያ ሰጥተዋል ። አቶ ተመስገን በሰጡት ማብራሪያ በሀገር አቀፉ የምክክር ኮሚሽን ማቋቋሚያ አዋጅ ላይ በመግቢያው የተገለጸውን ጉዳይ መሠረት በማድረግ ልዩነቶች መኖራቸውንና ለምክክሩ ምክንያት መሆናቸውን አብራርተዋል።…

Read More

የምክር ቤቱ አባላት ለጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ እስካሁን ያቀረቧቸው ዋና ዋና ጥያቄዎች

ከአሸባሪው ኦነግ ሸኔ ጋር የተደረገው ንግግር ያልተሳካው በምን ምክንያት ነው፤ በአማራ ክልል የተወሰደው ህግ የማስከበር እርምጃ በምን ደረጃ ላይ ይገኛል፤ የአማራ ክልል ነባራዊ ሁኔታ ከውጭ ሃይሎች ጣልቃ ገብነት ምን ያህል የጸዳ ነው፤ መንግስት የተዛቡ ችግሮችን ለማረምና አሰባሳቢ ትርክት ለመገንባት እየተሰሩ ያሉ ስራዎችን የተመለከተ ማብራሪያ ቢሰጥ፤ በመንግስትና በፓርቲ ውስጥ ያሉ ዋልታ ረገጥ አስተሳሰቦች ያላቸው ተዋንያንን ለማስተካከል…

Read More

በምዕራብ ኦሞ ዞን የተቀናጀ የተፋሰስ ልማት ሥራ በጋችት ወረዳ በይፋ ተጀመረ

በምዕራብ ኦሞ ዞን የዘንድሮው የተቀናጀ የተፋሰስ ልማት ሥራ በጋችት ወረዳ ቤሩ ቀበሌ የክልል እና የዞን የወረዳ ከፍተኛ አመራሮች በተገኙበት ዞናዊ ማስጀመሪያ በዛሬ በይፋ ተጀምሯል። የተፋሰስ ልማት ሥራው “የአፈር ጥበቃ ስራችን ለብልፅግናችን” በሚል መሪ ሃሳብ በሁሉም የገጠር ቀበሌዎች ላይ እየተካሄደ መሆኑ ተገልጿል። የክልል እና የዞኑ ከፍተኛ አመራሮች ጨምሮ የወረዳ ከፍተኛ የመንግስት የስራ ሃላፊዎች የተፋሰስ ስራዎችን አስጀምረዋል።…

Read More

የብልጽግና ፓርቲ 5ኛ ዓመት የምስረታ በዓል በተለያዩ ዝግጅቶች በሸካ ዞን ተከበረ

የሸካ ዞን ብልጽግና ፓርቲ ቅ/ጽ/ቤት የሀሳብ ልዕልና ለሁለንተናዊ ብልፅግና” በሚል መሪ ቃል የብልፅግና ፓርቲ 5ኛ ዓመት የምስረታ በዓል በልዩ ልዩ ዝግጅት በደማቅ ሁኔታ በቴፒ ከተማ እየተከበረ ይገኛል። በበዓሉ ላይ ተገኝተው መልዕክት ያስተላለፉት የዞኑ በብልፅግና ፓርቲ ቅ/ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ አለማየሁ አለሙ እስካሁን የተመዘገቡ ስኬቶችን በማስፋትና ክፍተቶችን በማረም ለሁለንተናዊ ብልፅግና መረጋገጥ መትጋት ያስፈልጋል ብለዋል። ለብልፅግና ፓርቲ 5ኛ…

Read More