የኢትዮጵያ ማንሰራራት ከትራንስፖርትና ሎጅስቲክስ ጋር የተሳሰረ ነው – ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን
የኢትዮጵያ ማንሰራራት ከትራንስፖርትና ሎጅስቲክስ ዘርፍ ማንሰራራት ጋር የተሳሰረ ነው አሉ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ፡፡ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ በኢትዮ-ጂቡቲ የምድር ባቡር ትራንስፖርት አክሲዮን ማኅበር የሰራተኞች ቀን በዓል ላይ ባስተላለፉት መልዕክት፥ የኢትዮ-ጂቡቲ የምድር ባቡር የኢትዮጵያውያን የአሸናፊነት ውጤት ነው ብለዋል፡፡ የኢትዮ-ጂቡቲ የምድር ባቡር የኢትዮጵያ ወጪና ገቢ ንግድ ዋና መተላለፊያ መስመር መሆኑን ጠቅሰው፥ መስመሩን ተከትለው በርካታ ከተሞች መቆርቆራቸውንና…
