በቀጣናው የምግብ ዋስትናን ለማረጋገጥ ለሚደረጉ ጥረቶች ድጋፍ ይደረጋል -ኢጋድ
በቀጣናው የምግብ ዋስትናን፣ የግብርና ምርታማነት ለማረጋገጥ ለሚደረጉ ጥረቶች ድጋፍ እንደሚያደርግ የምስራቅ አፍሪካ የልማት በይነ መንግስታት ባለስልጣን (ኢጋድ) አስታወቀ። የኢጋድ የመስኖ ስትራቴጂ ጥናት ማረጋገጫ ወርክሾፕ በአዲስ አበባ በመካሄድ ላይ ሲሆን በመድረኩ የቀጣናው አባል ሀገራት ተወካዮች እየተሳተፉ ይገኛሉ። በኢጋድ የኢኮኖሚ ትብብር እና ቀጣናዊ ትስስር ዳይሬክተር ሞሄለዲን ኤልቶሀሚ በዚሁ ወቅት እንዳሉት ቀጣናው ተደጋጋሚ ድርቅንና የውሃ አቅርቦት ችግሮችን እየተጋፈጠ…
