የማህበረሰቡን የልማት ጥያቄዎች ለመመለስ የተቀናጀ ተግባር እያከናወነ እንደሚገኝ የኮንታ ዞን አስተዳደር አስታወቀ።
የኮንታ ልማት ማህበር በውስጥ አቅም በተሰበሰበ ከ2 መቶ 15 ሚሊየን ብር በላይ የገዟቸው 5 የግንባታ ማሽነሪዎችን እና ኢሞታ አዳሪ ትምህርት ቤት ዛሬ በይፋ አስመርቋል። በመረሃ ግብሩ ላይ የዞኑ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ታከለ ተስፉ እንደገለጹት ልማት ማህበሩ በመንግስት ያልተሸፈኑ የተለያዪ የልማት ሥራዎችን በማከናወን ህብረተሰቡን ተጠቃሚ እያደረገ ይገኛል ብለዋል። በመንግስት ያልተሸፈኑ የልማት ክፍተቶችን ለማሟላት ልማት ማህበሩ የተቀናጀ…
