የኢትዮጵያ የስንዴ ልማት ስኬት ለአፍሪካ ምሳሌ የሚሆን ነው – ኦሊሴጉን ኦባሳንጆ
ኢትዮጵያ በስንዴ ልማት ያስመዘገበችው ስኬት ለተቀሩት የአፍሪካ ሀገራት ምሳሌ የሚሆን ነው አሉ የቀድሞ የናይጄሪያ ፕሬዚዳንት ኦሊሴጉን ኦባሳንጆ። ኦሊሴጉን ኦባሳንጆ በናይጄሪያ አቡጃ እየተካሄደ በሚገኘው 32ኛው የአፍሪኤግዚም ባንክ ዓመታዊ ጉባኤ ላይ ባደረጉት ንግግር፥ በአፍሪካ ሁለንተናዊ ዕድገት ለማስመዝገብ ብቃት ያለው አመራር መስጠት አስፈላጊ እንደሆነ አንስተዋል፡፡ አፍሪካ አህጉራዊ የግብርና አብዮት እንደሚያስፈልጋት ጠቁመው፥ ለዚህም ኢትዮጵያ በስንዴ ልማት ያስመዘገበችው ስኬት ለተቀሩት…
