የብልፅግና ፓርቲ የ2017 በጀት ዓመት የመጀመሪያ ሩብ ዓመት ዕቅድ አፈፃፀም ግምገማ በአሶሳ ከተማ እየተካሄደ ነው።
በመድረኩ ላይ የተገኙት የብልጽግና ፓርቲ ምክትል ፕሬዚዳንት አደም ፋራህ፤ በመድረኩ ባለፉት 3 ወራት በፓርቲው የተከናወኑ ዋና ዋና ተግባራት በስፋት የሚገመገሙ መሆኑን ጠቁመዋል። በመድረኩ በፓርቲ ደረጃ ላሉ አደረጃጀቶች የተሰጡ ሥልጠናዎች አጠቃላይ ሁኔታ ምን እንደሚመስልም የሚዳሰስ ይሆናል ነው ያሉት። በመቀጠል ፓርቲው ያዘጋጀው የአመራር ልማት ረቂቅ ፖሊሲ ላይ ውይይት በማድረግ እንዲዳብር ይደረጋል ብለዋል። ረቂቅ ፖሊሲው ጠንካራ ፓርቲ፣ ጠንካራ…
