ጠቅላይ ሚኒስትሩ ከምክር ቤት አባላት ለቀረቡላቸው ጥያቄዎች በሰጡት ምላሽና ማብራሪያ ካነሷቸው ዋና ዋና ጉዳዮች መካከል፡-
👉 ባለፉት ሦስት ወራት 180 ቢሊየን ብር ገቢ ሰብስበናል፡፡ ባለፈው ዓመት ተመሳሳይ ወቅት 109 ቢሊየን ብር ነበር የተሰበሰበው፡፡ የልዩነቱ ስፋት ለውጥ እንዳለ እና መንገዳችን ትክክል እንደሆነ አመላክች ነው፡፡ 👉 በፌደራል መንግሥት 900 ቢሊየን ብር በክልሎች ደግሞ 600 ቢሊየን ብር ገቢ መሠብሰብ ከተቻለ በአጠቃላይ 1 ነጥብ 5 ትሪሊየን ገደማ እንሰበስባለን ማት ነው፡፡ ይህም በቂ ባይሆንም ትልቅ…
