Trendings

Getenesh Gebeyehu

በግብርናው ዘርፍ በተለያዩ ፕሮግራሞችና ፕሮጀክቶች ድጋፍ የሚከናወኑ ተግባራት የግብርና ምርታማነት ለማሳደግ የሚኖረው ሚና ከፍተኛ በመሆኑ የተጀመሩ ሥራዎች ተጠናክሮ እንደሚቀጥሉ አቶ ማስረሻ በላቸው ገለጹ።

የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ግብርና ቢሮ SNV HORT LIFE 3 ፕሮግራም ጋር በመተባበር የአርሶ አደር የመስክ ትምህርት ቤት ተቋማዊ ማድረግ በሚያስችሉ ጉዳዮች ዙሪያ ከባለድርሻ አካላት ጋር በቦንጋ ከተማ ተወያይተዋል። በመድረኩም በፕሮግራሙ እስካሁን የተሰሩ ሥራዎችን ማጠናከር እና ቀጣይ መሻሻል በሚገቡ ጉዳዮች ላይ ከተሳታፊዎች ሀሳብ አስተያየቶች ተነስተው ሰፊ ውይይት ተደርጓል። የክልሉ ምክትል ርዕሰ መስተዳድር እና የግብርና…

Read More

በቡና ምርት ጥራት፣ አቅርቦት እና በግብይት ስርዓቱ ላይ በትኩረት በመስራት ቡናን ለማዕከላዊ ገበያ ለማቅረብ እየሰራ እንደሚገኝ የክልሉ ቡና ሻይ ቅመማ ቅመም ባለስልጣን አስታወቀ፡፡

ባለስልጣኑ የታጠበ ቡና ምርት አዘገጃጀት እና ጥራት አጠባበቅ ላይ ከካፋ ዞን ለተውጣጡ የግብርና ባለሙያዎች እና ኢንዱስትሪ ባለቤቶች በቦንጋ ከተማ ስለጠና ሰጥቷል። በስልጠናው በታጠበ ቡና ምርት ዝግጅትና ጥራት አጠባበቅ ፣ በቡና ግብይት አሰራር እንዲሁም የታጠበ ቡና ምርት አዘገጃጀት ላይ ትኩረት ያደረገ ነው። የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ቡና ሻይ ቅመማ ቅመም ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር አቶ አስራት…

Read More

በሚዛን አማን ከተማ አስተዳደር በ2018 የበጀት ዓመት በአንደኛ ሩብ ዓመት የተከናወኑ ተግባራት ላይ ህዝባዊ የውይይት መድረክ እየተካሄደ ነው።

የውይይቱ ዓላማ በከተማ አስተዳደሩ በሁለቱም ዘርፎች በመንግስትና በፓርቲ የተከናወኑ ተግባራት ለነዋሪዎች ማሳወቅና ጠንካራና ውስንነቶችን በመለዬት በቀጣይ የሚሰሩ ስራዎችን በመለዬት በቀጣይ የሚሰሩ የልማት ስራዎችን ለማጠናከር መሆኑ ተገልጿል። የሚዛን አማን ከተማ አስተዳደር ከንቲባ ኢንጅነር ሰለሞን ሌዊ እንደተናገሩት ለአንድ ከተማ ዘላቂነት ያለው ልማትና ዕድገት እንዲመዘገብ ለማድረግ የህዝብ ተሳትፎና ተጠቃሚነት ማረጋገጥ ወሳኝ ነው ብለዋል። በዚህም በከተማዋ በሚሰሩ የልማትና የመልካም…

Read More

በካፋ ዞን የተለያዩ ከተማ አስተዳደሮች “የመልካም አስተዳደር ችግሮችን በመቅረፍ የኢትዮጵያን ማንሰራራይ እውን እናደርጋለን!” በሚል መሪ ሃሳብ ከነዋሪዎች ጋር ውይይት እየተካሄደ ነው።

መድረኮቹ በሁሉም ዘርፎች የተመዘገበዉን ለዉጥ በማስቀጠል የመልካም አስተዳደር ችግሮችን በዘላቅነት በመፍታት የህዝቡን ተጠቃሚነት በሁሉም ዘርፍ ማረጋገጥ በሚያስችሉ ጉዳዮች ላይ ያጠነጠነ ነው። የቦንጋ ከተማ አስተዳደር ውይይቱን የመሩት የዞኑ አስተዳዳሪ አቶ እንዳሻው ከበደ በከተማ አስተዳደሩ የተለያዩ የመልካም አስተዳደር ችግሮችን ለመቅረፍ መጠነ ሰፊ ተግባር መከናወኑን ገልጾ በዚህም ለህዝብ ድምፅ ትኩረት በመስጠት ማዘጋጃ ቤት ላይ ያደረገው የሪፎርም ስራና 13…

Read More

በኮንታ ዞን 18 አመራሮች ከኃላፊነት ተነሱ

በኮንታ ዞን አመራር ውጤታማነትን፣ ስነ ምግባርንና ዝግጁነትን መሠረት ባደረገ ጥብቅ ምዘና፣ በዞኑ የሚገኙ 71 አመራሮችን ከዞን እስከታችኛዉ መዋቅር የማንሳት፣ የማሸጋሸግና አዲስ ምደባ ማከናወኑን የዞኑ ብልጽግና ፓርቲ ቅ/ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ገዛኸኝ ገዝሙ ተናግረዋል። በዚህም መሰረት፡ 18 አመራሮች ከኃላፊነት ተነስተዋል። 25 አመራሮች ሽግሽግ ተደርጓል። 28 አዳዲስ አመራሮች ወደ ኃላፊነት መጥተዋል። ይህ እርምጃ በተለይ ወጣቶችንና ሴቶችን ያገናዘበ መሆኑ…

Read More

በክልሉ የአርሶ አደሮች መስክ ትምህርት ቤት የግብርና ቴክኖሎጂ ሥርፀት ማዕከል እንዲሆን ሥራዎች እየተከናወነ ይገኛል፦አቶ ማስረሻ በላቸው

የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ግብርና ቢሮ SNV HORT LIFE 3 ፕሮግራም ጋር በመተባበር የአርሶ አደር የመስክ ትምህርት ቤት ተቋማዊ ማድረጊያ የውይይት መድረክ በቦንጋ ከተማ እያካሄደ ነው። በመድረኩ የክልሉ ምክትል ርዕሰ መስተዳድር እና የግብርና ቢሮ ኃላፊ አቶ ማስረሻ በላቸው በክልሉ (SNV HORT LIFE 3) ፕሮጀክት በ18 ወረዳዎች የሚሰራ ሲሆን ከዚህም በ11 ወረዳዎች በቀጥታ እና በቀሪ…

Read More

በዳውሮ ዞን 59 አመራሮች ከኃላፊነታቸው ተነሱ

በዳውሮ ዞን በቅርቡ በተደረገ ጥብቅ ግምገማ ላይ ተመስርቶ በተወሰደው እርምጃ ከዞን አስከታችኛዉ መዋቅር 59 አመራሮች ሙሉ በሙሉ ከኃላፊነታቸው የተነሱ ሲሆን፣ ሌሎች 55 አመራሮች ደግሞ የኃላፊነት ሽግሽግ ተደርጓል። የዞኑ ብልጽግና ፓርቲ ቅ/ጽ/ቤት ፖለቲካና ህዝብ ግንኙነት ኃላፊ አቶ ኢዮብ ቶማስ እንደገለጹት፣ ይህ እርምጃ የተወሰደው ያለፈውን ዓመት አፈጻጸም ከመዘነ በኋላ መጪውን ተልዕኮ በብቃትና በስነ ምግባር ሊያስፈጽም የሚችል ጠንካራ…

Read More

የኢትዮጵያ የሚዲያ ልህቀት ማዕከል ስራ ጀመረ

የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙሃን ባለስልጣን የመገናኛ ብዙሃንን አቅም ለማሳደግ በሚል ያቋቋመው የሚዲያ ልህቀት ማዕከል በይፋ ስራ ጀምሯል። በማስጀመሪያ መርሐ ግብሩ ላይ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አፈ ጉባኤ ታገሰ ጫፎ እንዳሉት፤ በሰላም፣ በመልካም አስተዳደር ዘርፍም ሆነ በኢኮኖሚ ጉዳዮች ላይ ወቅታዊና ትክክኛ መረጃ በማቅረብ መገናኛ ብዙሃን ሚናቸው የጎላ ነው። ሚዲያዎች ለማህበረሰብ እድገት የራሳቸውን ሚና በመጫወት የኢትዮጵያን እድገት ለማረጋገጥ…

Read More

የህዝብ ተጠቃሚነትን ማረጋገጥ ቀዳሚ ትኩረት መሆኑ ተገለጸ

በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል፣ የህዝብን ተጠቃሚነት ማረጋገጥን ማዕከል ያደረገ የክልልና የዞን ምክር ቤቶች የ2018 የመጀመሪያ ሩብ ዓመት አፈጻጸም ግምገማ በታርጫ ከተማ ተጀመረ። መድረኩን በንግግር የከፈቱት የክልሉ ምክር ቤት ዋና አፈ ጉባኤ የተከበሩ አቶ ወንድሙ ኩርታ፣ የምክር ቤት አባላት በየደረጃው የህብረተሰቡን ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ ከምንጊዜውም በላይ በትጋት እንዲሰሩ አሳስበዋል። “በሩብ ዓመቱ የታዩ ጠንካራ ጎኖችን በማስቀጠልና የታዩ…

Read More

የሕብረተሰብ ተሳትፎን ሁሉም ተቋማት ባህል አድርጎ በመስራት ውጤት ማስመዝገብ ይገባቸዋል። አቶ ፋጂዮ ሳፒ

የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ክልላዊ መንግስት የ2018 ዓ/ም የመሠረተ ልማት ክላስተር ተቋማት የ1ኛ ሩብ ዓመት አፈጻጸም እና የቀጣይ አቅጣጫዎች የተግባቦት መድረክ በሚዛን አማን ከተማ ተካሂዷል ። በዚህም የክላስተር ተቋሟት የሆኑት የክልሉ ትራንስፖርት እና መንገድ ልማት ፣ የከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን ፣ የውሃ፣ ማዕድንና ኢነርጂ ቢሮ እና አርብቶ አደርና ቆላማ አካባቢ ጉዳይ ቢሮዎች የ1ኛ ሩብ ዓመት ሪፖርታቸውን…

Read More