Trendings

የጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ አህመድ መልዕክት

በጽሕፈት ቤታችን ከተገኙት የአሜሪካ ረዳት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ክሪስቶፈር ቲ ላንዳው እና የዩኤስ አፍሪካ እዝ አዛዥ ጄነራል ዳግቪን አንደርሰን ጋር ተወያይተናል:: ቀጣይነት ያለው ትብብር እና መከባበርን አፅንዖት ለሰጠው ደማቅ እና ገንቢ ውይይታችን ምስጋናዬን አቀርባለሁ::

Read More

የሚዛን አማን አውሮፕላን ማረፊያ ግንባታ 62 በመቶ መጠናቀቁ ተገለጸ::

የሚዛን አማን አውሮፕላን ማረፊያ ግንባታ 62 በመቶ መጠናቀቁን ግንባታውን የሚያከናውነው ሥራ ተቋራጭ አስታወቀ። የአውሮፕላን ማረፊያውን በተያዘለት ግንባታ ለማጠናቀቅ የአካባቢው የአየር ጸባይ ፈተና መሆኑን ተቋራጩ ገልጿል። የሳምሶን ቸርነት ስራ ተቋራጭ ስራ አስኪያጅ እንጂነር ኢዮብ ሞላ በሥፍራው ለሚገኙት የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት ዘጋቢዎች እንደገለጹት፣ የአውሮፕላን ማርፊያው በ930 ሚሊዮን ብር በጀት እየተገነባ ነው። የአውሮፕላን ማረፊያው ከፍተኛ የህዝብ የልማት ጥያቄ…

Read More

ክልሉ እያካሄደ በሚገኘው የትምህርት ለትውልድ የንቅናቄ ሥራ ተጨባጭ ለውጦች እየተመዘገቡ እንደሚገኝ የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ትምህርት ቢሮ አስታወቀ፡፡

በዘርፉ ዘላቂ የሆነ ውጤት እንዲመዘገብ ለማስቻል የድርሻቸውን እንደሚወጡ በክልሉ የኮንታ ዞን ነዋሪዎች ገልፀዋል። የትምህርት ልማት ሥራዎችን ውጤታማ ለማድረግ በመንግስት የተለያዩ የለውጥ ማዕቀፎች ተነድፈው ተግባራዊ እየተደረጉ ይገኛል። ማዕቀፎቹን ለመተግበር መንግስት በየደረጃው ለህዝብ ተሳትፎ ትኩረት ሰጥቶ በመንቀሳቀስ ባለፉት ጥቂት ጊዜያት አመርቂ ለውጦች ማስመዝገብ መቻሉን በኮንታ ዞን በኮንታ ኮይሻና አመያ ያነጋገርናቸው የትምህርት ባለሙያዎች እና ነዋሪዎች አረጋግጠዋል። በዞኑ ኮንታ…

Read More

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የኢንዱስትሪ ዘርፍን በተመለከተ የሰጡት ምላሽና ማብራሪያ:-

በኢንዱስትሪው ዘርፍ የነበረውን የውጭ ምንዛሬ አቅርቦት ችግር ለመቅረፍ መንግስት ጣልቃ በመግባት የኢኮኖሚ መሻሻያ አድርጓል፤ በዚህም ተጨባጭ ውጤት ተገኝቷል፣ የሀይል አቅርቦት ችግርን ለመቅረፍ በተከናወኑ ተግባራት በዘርፍ ኢነርጂ 100 ፐርሰንት ተደራሽ ማድረግ ተችሏል፣ ከአምናው ጋር ሲነፃፀር በኢንዱስትሪው ዘርፍ 50 በመቶ የሀይል አቅርቦት ጭማሪ ተደርጓል፣ ከግብዓት ጋር እንዲሁም ከኢንዱስትሪ መሬት አቅርቦት ጋር በተያያዘ መንግስት በርካታ ስራዎችን አከናውኗል፣ ኢትዮጵያ…

Read More

በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ቡና የቱሪዝም ማዕከል እንዲሆን በልዩ ትኩረት ይሰራል ተባለ

የክልሉ ደን፤ አካባቢ ጥበቃና የአየር ንብረት ለውጥ ቢሮ ከFOLUR ፕሮጀክት ከክልሉ ቡና ሻይና ቅመማቅመም ባለስልጣን ጋር በመተባበር የቡና ምርታማነት ማሻሻል ላይ ትኩረት ያደረገ የምክክር መድረክ በቦንጋ ከተማ አካሂዷል። በመድረኩ የተገኙት የክልሉ ምክትል ርዕሰ መስተዳድርና የግብርና ቢሮ ኃላፊ አማካሪ እና የግብርና ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ዮሐንስ መላኩ፤ በክልሉ ቡና እና የቅመማቅመም ምርቶች የማኅበረሰቡን ኑሮ ከመቀየር ባሻገር ለኢኮኖሚ…

Read More

የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ሥነ-ምግባርና ፀረ-ሙስና ኮሚሽን በሀገር አቀፍ ደረጃ 3ኛ ደረጃን በመያዝ ተሸለመ።

የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል የሥነ-ምግባርና ፀረ-ሙስና ኮሚሽን በ2017 የበጀት ዓመት የሥራ አፈፃፀሙ በሀገር አቀፍ ደረጃ ከሁሉም ክልሎችና የከተማ አስተዳደሮች ጋር ባደረገው ጠንካራ ውድድር 3ኛ ደረጃን በመያዝ ታላቅ ስኬት አስመዝግቧል። ይህ እውቅና የተሰጠው፣ ጥብቅ በሆነ ሀገር አቀፍ የአቻ ለአቻ ምዘናና ግምገማ ሲሆን፣ ኮሚሽኑ ላስመዘገበው ድንቅ ውጤት የማበረታቻ ሽልማትና ሰርተፍኬት ከኢፌዴሪ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ክቡር አቶ…

Read More

በተጠናቀቀው በጀት ዓመት በክልሉ የህዝብ የልማት ተጠቃሚነት የሚያረጋግጡ መጠነ ሰፊ ተግባራት ተከናውኗል።

በተጠናቀቀው በጀት ዓመት በክልሉ የህዝብ የልማት ተጠቃሚነት የሚያረጋግጡ መጠነ ሰፊ ተግባራት ተከናውኗል። አፈ-ጉባኤ የተከበሩ አቶ ወንድሙ ኩርታ የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል የፓርላማ ተወካዮች እና የክልል ምክር ቤት አባላት የክረምት ወራት የውክልና ስራዎች ማስጀመሪያ የምክክር መድረክ በቦንጋ ከተማ ተካሂዷል። በመድረኩ ተገኝተው ንግግር ያደረጉት የክልሉ ምክር ቤት ዋና አፈ-ጉባኤ የተከበሩ አቶ አቶ ወንድሙ ኩርታ፥ በተጠናቀቀው የ2017…

Read More

በምንዛሬ የሚገቡ ምርቶችን በሀገር ውስጥ በመተካት 3 ነጥብ 1 ቢሊየን ዶላር ማዳን ተቻለ::

ወደ ሀገር ውስጥ በውጪ ምንዛሬ የሚገቡ ምርቶችን በሀገር በቀል ምርቶች በመተካት 3 ነጥብ 1 ቢሊየን የአሜሪካ ዶላር ከብክነት ማዳን መቻሉን የኢንዱስትሪ ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡ ሚኒስቴሩ የ2016 በጀት ዓመት የ9 ወራት ዕቅድ አፈፃፀምን በተመለከተ ከሚኒስቴሩ ሥራ አስፈፃሚዎች እና ሠራተኞች ጋር እየተወያየ ነው፡፡ በዚህ ወቅትም የአምራች ኢንዱስትሪዎችን የማምረት አቅም ተግዳሮቶች ለመቅረፍ ከፍተኛ ጥረት በመደረጉ አበረታች ለውጥ መምጣቱ ተገልጿል።…

Read More

በገዜ ጎፋ ወረዳ በመሬት መንሸራተት አደጋ ተጨማሪ ጉዳት እንዳይደርስ ነዋሪዎችን በትምህርት ቤት የማስጠለል ሥራ እየተሰራ ነው

በጎፋ ዞን ገዜ ጎፋ ወረዳ በመሬት መንሸራተት አደጋ ተጨማሪ ጉዳት እንዳይደርስ ነዋሪዎች በትምህርት ቤት በጊዜያዊነት እንዲጠለሉ የማድረግ ሥራ እየተሰራ መሆኑን የዞኑ ፖሊስ አስታወቀ። በወረዳው ኬንቾ ቀበሌ ዛሬ ጠዋት ንጋት ላይ በተከሰተው የመሬት መንሸራተት አደጋ የሟቾች ቀጥር 55 መድረሱንም ፖሊስ ገልጿል። የጎፋ ዞን ፖሊስ አዛዥ ኢንስፔክተር ታረቀኝ አጥናፉ ለኢዜአ እንደገለጹት፣ ትናንት ሌሊት ለ5 ሰዓታት ሳያቋርጥ የጣለው…

Read More

በትምህርት ዘርፍ የሚደረጉ የድጋፋዊ ክትትል ስራዎች ለዘርፉ ውጤታማነት ጉልህ አስተዋጽኦ እንዳለው ተጠቆመ።

በክልሉ በትምህርት ዘርፍ ስራዎች በተደረገ የድጋፍና ክትትል ስራ የግብረ መልስ መድረክ ተካሂዷል። የክልሉ ምክር ቤት ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢዎች በዳውሮ፣ በኮንታ፣ በቤንች ሸኮና በካፋ ዞን በ16 ትምህርት ቤቶች ያደረጉትን የድጋፍና ክትትል ስራዎች ሪፖርት በዝርዝር አቅርበዋል። የግብረ መልስ መድረኩን የመሩት የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ምክር ቤት ዋና አፌ ጉባኤ የተከበሩ አቶ ወንድሙ ኩርታ በምክር ቤቱ ቀሚ…

Read More