Trendings

የ2018 ዓ.ም በተቀናጀ ተፋሰስ ልማት ከ272 ሺህ ሄክታር በላይ መሬት እንደሚለማ የክልሉ ግብርና ቢሮ አስታወቀ

‎የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ግብርና ቢሮ የ2018 ዓ.ም የተፋሰስ ልማት ስራዎችን ዉጤታማ ለማድረግ የቅድመ ዝግጅት ስራዎች እየተሰሩ መሆናቸዉ ተገልጿል። ‎የክልሉ ግብርና ቢሮ ምክትል ኃላፊ እና የተፈጥሮ ሀብት ልማትና መሬት አስተዳደር እና አጠቃቀም ዘርፍ ኃላፊ አቶ ዉብሸት ዘነበ እንደገለጹት የማህበረተሰብ የተቀናጀ ተፋሰስ ስራዎች ትግበራ በትኩረትና ከፍተኛ የህዝብ ንቅናቄ በተሳካ ሁነታ የሚከናወን እንዲሁም ልማትና ምርትና ምርታማነትን…

Read More

ምግብና ሥርዓተ-ምግብን በማሻሻል የቤተሰብ ብልጽግናን ለማረጋገጥ እየተሰራ መሆኑ ተገለጸ።ADSCD

‎ ‎በክልሉ ግብርና ቢሮ የእንስሳትና ዓሳ ሀብት ልማት ዘርፍ ከምግብ ሥርዓት ማጠናከሪያ ፕሮግራም ጋር በመተባበር ለእንስሳት እርባታ ባለሙያዎች የአሰልጣኞች ስልጠና በቦንጋ ከተማ እየተሰጠ ነው። ‎ ‎በስልጠናው መድረክ ተገኝተው ንግግር ያደረጉት በክልሉ ግብርና ቢሮ የእንስሳትና ዓሳ ሀብት ልማት ዘርፍ ኃላፊ አቶ ታመነ በቀለ ባለፉት አራት አመታት በሌማት ትሩፋት ዘርፍ የተከናወኑ ተግባራት የተሻለ መነቃቃት የታየባቸው ናቸው ብለዋል።…

Read More

የክልል ብሔረሰቦች ምክር ቤት መደበኛ ጉባኤውን ከመጋቢት 08/2018 ጀምሮ በቴፒ ከተማ እንደሚያካሂድ አስታወቀ

የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ምክር ቤት 4ኛ ዓመት 6ኛ መደበኛ ጉባኤውን በቴፒ ከተማ ላይ እንደሚያካሄድ የምክር ቤቱ ዋና አፈ ጉባኤ የተከበሩ አቶ ጌታቸው ኬኒ ገልፀዋል። በክልሉ በ2018 በጀት ዓመት ስድስት ወራት ፀጥታን ፣ የዝርፊያና የስርቆት ወንጀሎችን መከላከል እንዲሁም ከወሰን ጉዳዮች ጋር ተያይዞ የሚፈጠሩ አለመግባባቶችን ሰላማዊ በሆነ መንገድ እንዲፈቱ የማድረግ ስራዎች ላይ ምክር ቤቱ በትኩረት…

Read More

ትምህርት ሚኒስቴር የ2018 የትምህርት ዘመን ሪሜዲያል መግቢያ ነጥብ ይፋ አደረገ።

ትምህርት ሚኒስቴር በ2018 የትምህርት ዘመን የመንግስት ዩኒቨርሲቲዎችን በተፈጥሮ እና ማህበራዊ ሳይንስ ትምህርት መስኮች ከ49.5% በታች ያስመዘገቡ ነገር ግን ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን የሚያሟሉ ተማሪዎች የRemedial ፕሮግራም ተጠቃሚ መሆናቸውን አሳውቋል። 1. በሁሉም አማራጮች (በግል እና በመንግስት ተቋማት) የ Remedial ፕሮግራም ለመከታተል ተማሪዎች እንደተፈተኑት የትምህርት አይነት ብዛት 33% ከመቶ እና ከዚያ የተቆረጠ መሆኑን። 2. ከላይ በተራ ቁጥር 1…

Read More

የ “ታላቁ የአፍሪካ አረንጓዴ ግንብ ኢኒሼቲቭ” ላይ ያተኮረ ስብሰባ እየተካሄደ ነው

የ”ታላቁ የአፍሪካ አረንጓዴ ግንብ ኢኒሼቲቭ” (The great green wall initiative) የባለሙያዎች እና የአጋር አካላት ላይ ያተኮረ ስብስባ ዛሬ በአፍሪካ ህብረት መካሄድ ጀምሯል። በስብሰባው መክፈቻ ላይ የአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን የግብርና፣ ገጠር ልማት፣ ብሉ ኢኮኖሚ እና ዘላቂ ከባቢ አየር ኮሚሽን አመራሮች፣ የአባል አገራት ተወካዮች፣ ባለሙያዎች፣ የልማት አጋሮች እና ሌሎች ባለድርሻ አካላት ተገኝተዋል። እስከ ግንቦት 7 ቀን 2017…

Read More

innovation

በክህሎት ልማት እና በስራ ዕድል ፈጠራ ውጤታማ ስራዎችን ማከናወን ተችሏል የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ስራና ክህሎት ቢሮ የተጣለበትን ስትራቴጂያዊ ግቦችን ከማሳካት አንፃር ውጤታማ ስራዎችን ማከናወኑን አስታዉቋል፡፡ በህብረተሰቡ ውስጥ ዘመናዊ የመረጃ ቴክኖሎጂን በመዘርጋትና በማስፋፋት ለህብረተሰቡ አስፈላጊ መረጃዎችን እንዲያገኙ በማድረግ በክህሎት ልማት፣በስራ ዕድል ፈጠራ፣በሰላማዊ የኢንዱስትሪ ግኑኝነት እና በሙያቸዉ የበቁ ዘጎችን ከማፍራት አንፃር ዘርፈ ብዙ ስራዎች እየተሰራ…

Read More

ኢትዮጵያ በብሪክስ ውስጥ ተጠቃሚነቷ እንዲረጋገጥ የፖሊሲ አቅጣጫዎችን በጥናት ለመደገፍ እየተሰራ ነው

ኢትዮጵያ በብሪክስ ውስጥ በጋራ ተጠቃሚነት መርህ ተጠቃሚነቷ እንዲረጋገጥ የፖሊሲ አቅጣጫዎችን በጥናት ለመደገፍ እየተሰራ መሆኑን የውጭ ጉዳይ ኢንስቲትዩት ገለጸ። በኢንስቲትዩቱ የኤዥያና ፓሲፊክ ጉዳዮች ጥናትና ምርምር ዳይሬክተር ጄኔራል አንተነህ ጌታቸው(ዶ/ር) በኢትዮጵያ የውጭ ጉዳይ ፖሊሲ የጋራ ተጠቃሚነት መርህ አንዱ ነው ብለዋል። ይህንን ከግምት በማስገባት ኢትዮጵያ ብሪክስን መቀላቀሏ ብሔራዊ ጥቅምን ከማስከበር ጎን ለጎን የጋራ ተጠቃሚነትን በማረጋገጥ ከፍተኛ አስተዋጽዖ እንዳለው…

Read More

የኑሮ ውድነትን በተመለከተ

የኑሮ ውድነትን በዘላቂነት መቅረፍ የምንችለው ምርታማነትን በመጨመር ነው፡፡ የንግድ ስርዓቱን ማዘምንም ከፍተኛ ፋይዳ አለው፡፡ የኑሮ ውድነቱ እጅ አጠር ዜጎች ላይ ጫና እንዳይፈጥር መንግስት ከ300 እስከ 400 ቢሊዮን ብር የድጎማ በጀት መድቧል፡፡ ማዕድ ማጋራት፣ ትምህርት ቤት ምገባ እና እሁድ ገበያ መንግስት አቅመ ደካሞችን ለማገዝ የሚያደርገው ጥረት አካል ነው፡፡ በሀገር አቀፍ ደረጃም 249 ሺህ አቅመ ደካማ ዜጎች…

Read More

የዓለም አቀፍና ቀጣናዊ አጋር ድርጅቶች አመራሮች የሕዳሴ ግድብን ጎበኙ

የዓለም አቀፍ አጋር ድርጅቶችና ቀጣናዊ አጋር ድርጅቶች አመራሮች እንዲሁም የግድብ ደህንነት ባለሞያዎች የታላቁ ኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብን ጎብኝተዋል። በውሃና ኢነርጂ ሚኒስትር ዴዔታ አብርሃ አዱኛ (ዶ/ር) በተመራው የሕዳሴ ግድብ ጉብኝት መርሐ ግብር የተፋሰሱ ተጋሪ ሀገራት ኮሚሽነሮችና ከፍተኛ የሥራ ሃላፊዎች ተሳትፈዋል። በተጨማሪም የካናዳና የአውስትራሊያ ግድቦች ማህበር፣ የኖርዌይ የሀይድሮፓወር ማህበር እንዲሁም የዛምቢያ ዛምቤዚ ወንዝ ባለስልጣን አመራሮች መሳተፋቸው ተገልጿል። የጉብኝት…

Read More

የብልፅግና ፓርቲ ለ7ኛው ጠቅላላ ምርጫ የሚያደርገውን የይምረጡኝ ቅስቀሳ በቴፒ ከተማ አስተዳደር ስር በሚገኙ ሦስቱም ቀበሌዎች በደማቅ ሁኔታ አካሂዷል።

በዕለቱም የፓርቲው አባላትና ደጋፊዎች የለውጥ ዓመታቱን የልማትና የመልካም አስተዳደር ስኬቶች የሚያወሱ መልዕክቶችን በማስተጋባት በህብረት ቀበሌ፣በሰላም እና በአንድነት ቀበሌዎች ታላቅ የአደባባይ ቅስቀሳ አካሂደዋል ። ​በሰላም ቀበሌ ተገኝተው ንግግር ያደረጉት የቴፒ ከተማ ከንቲባ አቶ ገላቲያስ ሻሜ፤ ፓርቲው ሀገሪቱን መምራት ከጀመረበት ጊዜ አንስቶ አመርቂ ድሎች በሁሉም ዘርፍ ተከናውኗል ብለዋል። በተለይም በቴፒ ከተማ የነበረውን የፀጥታ ችግር በመፍታት የተሟላ ሰላም…

Read More