ላለፉት 4 ዓመታት ለተጨማሪ 490 ሺህ ነዋሪዎች የንፁህ መጠጥ ውሃ ማድረስ እንደተቻለ የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ውሃ ማዕድንና ኢነርጂ ቢሮ ገለፀ።
የቢሮ ሀላፊ የሆኑት ኢንጂነር በየነ በላቸው የንፁህ መጠጥ ውሃ ከፍተኛ ኢንቨስትመንት የሚጠይቅ በመሆኑ የተለያዩ አጋር አካላት ድጋፍ ተጠናክሮ መቀጠል እንዳለበት ጠይቀዋል። በክልሉ የንፁህ መጠጥ ውሃና ሌሎች መሰረት ልማት አነስተኛ እንደነበረ ነው ኢንጅነር በየነ በላቸው ከዝግጅት ክፍላችን ጋር በነበራቸው ቆይታ ወቅት የገለፁት። የክልሉ መንግስት ችግሩን ለመቅረፍ በወሰደው ልዩ እርምጃ በክልሉ የንፁህ መጠጥ ውሃና የሌሎች መሰረተ ልማት…
