የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላት ለጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ያነሷቸው ጥያቄዎች
ፍትሃዊ የሆነው የኢትዮጵያ ህዝብ የዘመናት የባህር በር ጥያቄ በሰላማዊ፣ ህጋዊና ዲፕሎማሲያዊ በሆነ መንገድ ምላሽ እንዲያገኝ የተጀመረው ሂደት በምን ደረጃ ላይ ይገኛል? ጎረቤቶቻችንና አፍሪካዊያን ወንድሞቻችን የባሕር በር ጥያቄውን ፍትሃዊነት እንዲረዱትና እንዲያግዙን፣ ወዳጅ ሀገራት ዓለም አቀፍ ተቋማት ተገቢውን ድጋፍ እንዲያደርጉ ምን እየተሰራ ነው? መንግስት ደሀ ተኮር ሪፎርም አራማጅ ነኝ እያለ የመንግስት ሰራተኛውንና ዝቅተኛ የማህበረሰብ ክፍሎችን ኑሮ ለማሻሻል…
