የዋጋ ግሽፈቱ ወደ 14.4.% ዝቅ ብሏል:: ምግብና ምግብ ነክ በሆኑ ምርቶች ላይ ግሽፈቱ ወደ 12% ወርዷል፦ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አብይ አህመድ
በበጀት ዓመቱ የዋጋ ግሽፈት በ2016 በጀት ዓመት ከነበረው 22% ወደ 14.4% መውረዱንና ከዚህ ውስጥ ምግብና ምክብ ነክ የሆኑ ሸቀጦች ግሽፈት ወደ 12% መውረዱን ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ (ዶ/ር) አስታወቁ፡፡ ጠቅላይ ሚኒስትሩ መንግስት ከብሔራዊ ባንክ ዓመቱን ሙሉ ብድር ሳይወሰድ ዓመቱን ማጠናቀቁ፣ በፊስካልና የገንዘብ ፖሊሲ እንዲሁም የውጭ ምንዛሬ አስተዳደር ማሻሻያ ላይ የተወሰደው እርምጃ የዋጋ ግሽፈትን ለመቆጣጠር ከፍተኛ…
ከምንም ተነስተው ለከተማ ቤት ባለቤትነት የበቁት የ’አቦ’ ቡና አምራቾች የስኬት ታሪክ
በአንድ ወቅት መሠረታዊ ፍላጎታቸውን ለማሟላት ይቸገሩ የነበሩ የዳውሮ ዞን አርሶ አደሮች፣ ዛሬ በቡና ልማት ተደራጅተው ህይወታቸውን ከመቀየር አልፈው በከተማ ውስጥ ቤት እስከመግዛት የደረሰ የስኬት ጉዞ ላይ መሆናቸውን አስታወቁ። ይህ ታሪክ የመደራጀት ኃይልና የሥራ ትጋት ምን ያህል ለውጥ እንደሚያመጣ በተግባር ያሳየው የ”አቦ ቡና አምራቾች ህብረት ሥራ ማህበር” ነው። የስኬቱ መነሻ ታሪኩ የሚጀምረው 20 አርሶ አደሮች (10ሩ…
የምግብ ስርዓት እና ስርዓተ ምግብ ተግባራትን ከገጠር ልማት ኮሪደር ጋር በማስተሳሰር መምራት ይገባል ። ኢንጂነር ነጋሽ ዋጌሾ (ዶ/ር ኢ/ር)
የምግብ ስርዓት እና ስርዓተ ምግብ ተግባራትን ከገጠር ልማት ኮሪደር ጋር በማስተሳሰር መምራት እንደሚገባ ዶክተር ኢንጂነር ነጋሽ ዋጌሾ ተናገሩ። የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል መንግስት የምግብ ስርዓት እና ስርዓተ ምግብ መዋቅራዊ አደረጃጀት ለመፍጠር የሚያስችል የንቅናቄ መድረክ በቦንጋ ከተማ ተደርጓል። በምክክር መድረኩ የተገኙት ርዕሰ መስተዳድር ዶክተር ኢንጂነር ነጋሽ ዋጌሾ በምግብ ስርዓት እና ስርዓተ ምግብ የተከናወኑ ተግባራት በተሻለ…
በሰንደቅ ዓላማ ስር ሆነን ሀገራዊ መግባባትና ህብረ ብሄራዊ አንድነትን ማፅናትን ያስፈልጋል፦ አቶ ታከለ ተስፉ
በኮንታ ዞን 18ኛው የሰንደቅዓላማ ቀን በዓል በተለያዩ ሁኔቶች ተከብሯል። የዕለቱን መልዕክት ያስተላለፉት የኮንታ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ ታከለ ተስፉ ብሄራዊ የሰንደቅዓላማ ቀን በዓል ሲከበር ለሰንደቅ ዓላማ የሚገባውን ክብር በመስጠት ዜጎች የጋራ ዕሴቶቻቸውን እንዲያጠናክሩና ሀገራዊ አንድነትና መግባባትን ለመፍጠር ያለመ እንደሆነ ገልፀዋል። ሰንደቅ ዓላማ ዜጎች ለሀገራቸው ያላቸውን ፍቅር የሚያሳዩበትና የማንነታቸው መገለጫ ነው ያሉት ዋና አስተዳዳሪው የኢትዮጵያ ሰንደቅ…
ማሽቃሮ ባሮ ለሠላም ግንባታ ስራ የጎላ ፋይዳ አለው፦ ርዕሰ መስተዳድር ኢንጅነር ነጋሽ ዋጌሾ (ዶ/ር)
የሸካቾ ብሔረሰብ የዘመን መለወጫ (ማሽቃሮ ባሮ) በተለያዩ ባህላዊ ክዋኔዎች ታጅበው በአንድራቻ ወረዳ፣ ጌጫ ከተማ እየተከበረ ይገኛል። በበዓሉ የተገኙት የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ርዕሰ መስተዳድር እንጂነር ነጋሽ ዋጌሾ (ዶ/ር) ማሽቃሮ ባሮ፥ የተጣሉ የሚታረቁበት፣ የተራራቁ የሚጠያየቁበት እንዲሁም እውነተኛ ፍትህ የሚረጋገጥበት በመኾኑ ለሠላም ግንባታ የጎላ ፋይዳ አለው ብለዋል። የለውጡ መንግሥት የህዝቦችን የጋራ ማንነት፣ ታሪክና ባህል በማልማትና በመጠበቅ…
የሸበሌ ሪዞርት ፕሮጀክት የመጀመሪያ ምዕራፍ ግንባታ ተጠናቀቀ
የፌዴራል መስኖና ቆላማ አካባቢ ሚኒስትር እና የፕሮጀክቱ ዋና ሥራ አስኪያጅ አብርሃም በላይ (ዶ/ር)፣ ከሶማሊ ክልል የከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን ቢሮ ኃላፊ አቶ አህመድ ሹክሪና ከሌሎች ከፍተኛ አመራሮች ጋር በመሆን የተጠናቀቁ የፕሮጀክት ሥራዎች ተዘዋውረው ጎብኝተዋል። ኃላፊዎቹ በጉብኝታቸው ወቅት የሸበሌ ሪዞርት ፕሮጀክት የመጀመሪያ ምዕራፍ ግንባታ መጠናቀቁን ያረጋገጡ ሲሆን፣ ለምረቃ ሥነ ሥርዓት እየተደረገ ያለውን ዝግጅትም ተመልክተዋል። በተጨማሪም፣ በፕሮጀክቱ ግንባታ…
በቦንጋ ዩኒቨርሲቲ እየተከናወኑ ያሉ የግብርናና ተፈጥሮ ሀብት ጥበቃ ስራዎች ተጠናክሮ መቀጠል እንደሚገባ አፈጉባኤዎች ተናገሩ
በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል አዘጋጅነት እየተካሄደ ባለው የጋራ ፎረም እየተሳተፉ የሚገኙ የክልሎች እና ከተማ አስተዳደር አፈጉባኤዎች በቦንጋ ዩኒቨርሲቲ እየተከናወኑ ያሉ የግብርናና የተፈጥሮ ሀብት ጥበቃ ስራዎች ተጠናክሮ መቀጠል እንደሚገባእንደሚገባ ተናግረዋል። የፎረሙ ተሳታፊ አፈጉባኤዎች በቦንጋ ዩኒቨርስቲ የሙዝ ልማት፣ የሌማት ትሩፋት አንዱ አካል የሆነውን የከብቶች እርባታ፣ የአትክልትና ፍራፍሬ ልማት ስራዎች እና በመማር ማስተማሩ ዘርፍ የቴክኖሎጂ ሽግግር ስራዎች…
ኢትዮጵያ የተዘጋባት በር በመከፈቱ ለዘርፉ ትልቅ ዕድል ነዉ – አለሙ ስሜ (ዶ/ር)
ኢትዮጵያ የተዘጋባት በር በመከፈቱ ለዘርፉ ትልቅ ዕድል መሆኑን የትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ ሚኒስትር ዓለሙ ስሜ (ዶ/ር) ገለጹ፡፡ የትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ ሚኒስቴር የ2016 በጀት ዓመት የመጀመሪያ አጋማሽ የሴክተር አፈጻጸም በወላይታ ሶዶ ከተማ እየገመገመ ነው፡፡ ዓለሙ ስሜ(ዶ/ር) በወቅቱ፥ ትራንስፖርት እና ሎጂስቲክስ የሁሉም ዘርፎች ደም ስር በመሆኑ በጋራ ልንሠራ ይገባል ነው ያሉት። በዚህም ባለፉት ጊዜያት በትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ ዘርፍ የተሳኩ ተግባራት መፈጸማቸውን…
ጉባኤው በአፍሪካ ጉዳዮች ላይ የጋራ ድምጽ ማሰማት የሚቻልበትን ዕድል ማመቻቸት ነው
የአፍሪካ ማኅበራዊ ሚዲያ ተፅዕኖ ፈጣሪዎች ጉባዔ (ASMIS) ዋነኛ ዓላማም በተፅዕኖ ፈጣሪዎች መካከል ጠንካራ ትብብር በመፍጠር በአፍሪካ ጉዳዮች ላይ የጋራ ድምጽ ማሰማት የሚችሉበትን ዕድል ማመቻቸት እንደሆነ የፐልስ ኦፍ አፍሪካ አስተባባሪ አቶ በረከት ሲሳይ ገለጹ። የአፍሪካውያንን አጀንዳ ለማስረፅና የጋራ ድምፅን ለማሰማት ዕድል የሚፈጥር መሆኑንም አክለዋል። ፐልስ ኦፍ አፍሪካ (Pulse of Africa-POA) ከ ኤ.ጂ.ኤ የቴክኖሎጂ ኢንተርፕራይዝ (AGA-Tech) ጋር…
