ፍትሃዊ የልማት ስርጭትና ተደራሽነትን ለማረጋገጥ በተሰጠው ትኩረት ተጨባጭ ለውጥ እየተመዘገበ ነው። ኢንጂነር ነጋሽ ዋጌሾ (ዶ/ር)
በክልሉ ፍትሃዊ የልማት ስርጭትና ተደራሽነትን ለማረጋገጥ በተሰጠው ትኩረት ተጨባጭ ለውጥ እየተመዘገበ መሆኑ የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ርዕሰ መስተዳድር ኢንጅነር ነጋሽ ዋጌሾ (ዶ/ር) ገለጹ። ርዕሰ መስተዳድሩ ይህንን ያሉት በክልሉ ምዕራብ ኦሞ ዞን ቱም ከተማ የተገነባውን የንጹህ መጠጥ ውሃ መርቀው በከፈቱበት ወቅት ነው። የክልሉ መንግሥት የህዝቡን መሠረታዊ የልማት ጥያቄዎች ለመፍታት ከመቼውም ጊዜ በተሻለ ትኩረት አድርገው እየሰራ…
