ዘንድሮ 23 ሚሊዮን ኢትዮጵያውያን ከሴፍቲኔት ተረጂነት ወጥተዋል – ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)
በዚህ ዓመት ብቻ 23 ሚሊዮን ኢትዮጵያውያን ከሴፍቲኔት ተረጂነት መውጣታቸውን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ገለፁ፡፡ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የመንግስትን የ2017 የዕቅድ አፈጻጸም አስመልክቶ ከምክር ቤቱ አባላት ለተነሱ ጥያቄዎች ምላሽና ማብራሪያ እየሰጡ ይገኛል፡፡ ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማብራሪያቸው፤ በዚህ ዓመት ብቻ 23 ሚሊዮን ኢትዮጵያውያን ከሴፍቲኔት ተረጂነት መውጣታቸውን ተናግረዋል፡፡ ይህ የማንሰራራት ትልቁ ማሳይ ነው ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፤…
