የቱሪዝም መዳረሻዎችን በመለየትና በመልማት ዘርፉን ወደ ተሻለ ደረጃ ለማሳደግ በልዩ ትኩረት እየሠራ ነው፦ የካፋ ዞን ባህል ቱሪዝምና ስፖርት መምሪያ
ኢትዮጵያ በርካታ ሰው ሠራሽና የተፈጥሮ የቱሪስት መስህቦች ያሏት አገር ነች፡፡ ያሏትን የተፈጥሮ ሀብቶች፣ ታሪካዊ ቅርሶች እንዲሁም የማይዳሰሱ ትውፊቶች በአግባቡ ለመጠቀም ፖሊሲዎችን እንደ አዲስ በመከለስ በዘርፉ ለውጥ ለማምጣት እየታተረች ትገኛለች፡፡ እነዚህን በርካታ የቱሪዝም መዳረሻ ቦታዎች በአግባቡ በማልማት ከዘርፉ የሚፈለገውን ያህል ኢኮኖሚዊ ጥቅም ማግኘት እንደሚያስፈልግ ይታመናል፡፡ በተለይ ቱሪዝም ትልቅ ኢኮኖሚያዊ ፋይዳ ያለው ዘርፍ መሆኑ በተደጋጋሚ ይነገራል፡፡ የቱሪዝም…
