በካፋ ዞን፣ጎባ ወረዳ የህዝብ የልማት ተጠቃሚነት የሚያሳድጉ ተግባራት እየተከናወነ መኾኑ ተገለጸ
የወረዳው ዋና አስተዳዳሪ አቶ ታረቀኝ ታደሰ ከክልሉ የመንግሥት ኮሙኒኬሽን ጋር በነበራቸው ቆይታ የህዝብ የልማት ተጠቃሚነትን የሚያሳድጉ በርካታ ተግባራት በወረዳው እየተከናወነ መኾኑን ተናግረዋል። ወረዳው፣ በዞኑ ከሚገኙ ወረዳዎች ሰፊ የልማት አቅም ያለው ወረዳ መኾኑን የጠቆሙት አቶ ታረቀኝ ለግብርናና ለቅመማ ቅመም ልማት ሰፊ አቅም ያለው እንደኾነ አስረድተዋል። ወረዳው በተለይም ለቡና ምርት ተስማሚ የአየር ፀባይና ስነምህዳር ያለው አከባቢ መኾኑን…
