የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ምክርቤት 6ኛ ዙር 4ኛ ዓመት የስራ ዘመን 8ኛ መደበኛ ጉባኤ ከሰዓት በኋላ ቀጥሎ ውሏል።
በምክርቤቱ ጉባኤ ላይ የክልሉ መንግስት ርዕሰ መስተዳድር ዶክተር ኢንጂነር ነጋሽ ዋጌሾ የ2017 በጀት ዓመት አፈጻጸም ሪፖርት አቅርበዋል። ርዕሰ መስተዳድሩ ባቀረቡት የአስፈጻሚ አካላት ሪፖርት ላይ ከምክርቤት አባላት አስተያየት እና ጥያቄዎች ቀርበዋል። የምክር ቤት አባላቱ የክልሉ መንግስት አስፈጻሚ አካላት አፈጻጸም ከጊዜ ወደ ጊዜ ከፍ ያለ፣የሚታይ ለዉጥ ያለበትና የተሻለ አፈጻጸም የተመዘገበት በጀት ዓመት ነዉ ስሉ አስተያየታቸውን ሰጥተዋል። የምክርቤት…
