የኢትዮጵያን ሁለንተናዊ ለውጥ በማረጋገጥ የአድዋ ድልን ማጽናት እንደሚገባ ተገለጸ
129ኛው የአድዋ ድል መታሰቢያ በዓል “ዓድዋ የጥቁር ሕዝቦች ድል!” በሚል መርህ ቃል በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል በቦንጋ ከተማ በድምቀት ተከብሯል። በዓሉን በሚመለከት በቀረበው ፓናል ውይይት ሀሳብ የሰጡት የክብረ በዓሉ ተሳታፊዎች የኢትዮጵያን ሁለንተናዊ ለውጥ በማረጋገጥ የአድዋ ድልን በትውልድ ውስጥ ማጽናት እንደሚገባ ተናግረዋል። አድዋ የመደማመጥና የመከባበር እንዲሁም በአንድነት የመቆም ውጤት መሆኑን የጠቆሙት የመድረኩ ተሳታፊዎች የአሁኑ ትውልድ፥…
