ብሔራዊ ዳታ – የማይበገር ሉዓላዊነት
በዘመናዊው ዓለም “ዳታ” ወይም “መረጃ” የኃይል ምንጭ፣ የፖሊሲ አቅጣጫ መለኪያ እና የኢኮኖሚ ጥንካሬ ማረጋገጫ ሆኗል። ብሔራዊ ዳታ፣ የአንድ ሀገር ዜጎች ማንነትን፣ የሀብት ክምችትን፣ የደኅንነት ምሥጢራትን፣ የማኅበራዊ አገልግሎቶችን እና የኢኮኖሚ እንቅስቃሴዎችን የሚያጠቃልል ሰፊ እና ስትራቴጂያዊ የዲጂታል ቋት ነው። ይህ መረጃ የሀገርን የልማት ሁኔታ የሚወስን፣ አደጋዎችን አስቀድሞ ለመከላከል የሚያስችል እና ለወደፊት ትውልድ የሚተላለፍ የዲጂታል ቅርጽ ያለው ብሔራዊ…
