“ኢትዮጵያ ውስጥ ሰው ጋዜጠኛ ወይም ፖለቲከኛ ስለሆነ አይታሰርም”፦ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ተገኝተው በሰጡት ማብራሪያ እንደገለጹት፤ ኢትዮጵያ ውስጥ ሰው ጋዜጠኛ ወይም ፖለቲከኛ ስለሆነ አይታሰርም፡፡ ወደ ፊትም አይታሰርም የፖለቲካ አውዱ ሊሰፋ ይገባል፡፡ በሰዎች መታሰር ኢትዮጵያ ምንም ትርፍ አታገኝም ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፤ ግን ደግሞ ህግ መከበርና የህግ የበላይነት መከበር አለበት ብለዋል፡፡ ስልጣን ካልሰጣችሁን፣ ስንታሰር ካልፈታችሁን ምን ዲሞክራሲ አለ ከተባለ እንደዚህ…
