የ24 ዓመቱ የማራቶን ክብረ ወሰን ባለቤት አትሌት ኬልቪን ኪፕቱም ከዚህ ዓለም በሞት ተለየ::
የ24 ዓመቱ የማራቶን ክብረ ወሰን ባለቤት ኬንያዊው አትሌት ኬልቪን ኪፕቱም በመኪና አደጋ ከዚህ ዓለም በሞት መለየቱን የዓለም አትሌቲክስ አስታወቀ። ኪፕቱም ባለፈው ጥቅምት ወር ቺካጎ ውስጥ በተደረገ የማራቶን ውድድር 2:00:35 በሆነ ሰዓት በመግባት የዓለም ክብረ ወሰን መስበሩ ይታወሳል። ይኸው ክብረ ወሰን ባለፈው ሳምንት መጽደቁም ይታወቃል። አትሌቱ እና ሩዋንዳዊ አሠልጣኙ ጌርቫይስ ሐኪዚማና ሕይወታቸው ያለፈው ኤልዶሬት ካፕታጋት በተባለ…
