ከስራ ዕድል ፈጠራ አኳያ የክልሉ መንግስት በሰጠው ልዩ ትኩረት ከባለድርሻ አካላት ጋር በመቀናጀት ውጤታማ ተግባራትን እያከናወነ እንደሚገኝ የስራና ክህሎት ቢሮ አስታወቀ።
የቢሮው ሀላፊ ዶ/ር ዐብይ አንዴሞ ቢሮው በክልሉ በ2018 በጀት አመት 10 ወራት ውስጥ የዜጎችኝ ተጠቃሚነት የሚያረጋግጡ ተግባራት ማከናወኑን ተናግረዋል። ሀላፊው አክለውም ከስራ ዕድል ፈጠራ አኳያ በግብርና፣በኢንዱስትሪና አገልግሎት ዘርፎች በአጠቃላይ ለ62 ሺ 72 ዜጎች የስራ ዕድል መፈጠሩንም አብራርተዋል። የቢሮው ምክትል ሀላፊና የስራ እድል ፈጠራና ኢንተርፕራይዝ ልማት ዘርፍ ሀላፊ አቶ ዳዊት ወንድሙ በበኩላቸው ቢሮው ከፋይናንስ አቅርቦት አንፃር…
