Trendings

በሌማት ትሩፋት ስራዎች አስደናቂ ውጤቶች ተመዝግበዋል – ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር)

በሌማት ትሩፋት ስራዎች አስደናቂ ውጤቶች መመዝገባቸውን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ገለጹ። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) ከምክር ቤት አባላት ለተነሱላቸው ጥያቄዎች ምላሽና ማብራሪያ እየሰጡ ይገኛሉ። የሌማት ትሩፋት ስራዎችን በተመለከተ በሰጡት ምላሽና ማብራሪያ እጅግ ተስፋ ሰጪ ውጤቶች እየተመዘገቡ መሆኑን ገልጸዋል። አዲስ አበባን ጨምሮ በተለያዩ አካባቢዎች የተጀመሩ የሌማት ትሩፋት ስራዎች አበረታች መሆናቸውን አንስተዋል። በእንቁላል፣ በወተት፣ በስጋ ምርት…

Read More

በመኸር አዝመራ ከ400 ሺህ ሄክታር በላይ ማሳ በማልማት ከ17 ሚሊዮን ኩንታል በላይ ምርት ለማግኘት እየተሰራ መሆኑን የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ምክትል ርዕሰ-መስተዳድርና የግብርና ቢሮ ኃላፊ አቶ ማስረሻ በላቸው ገለጹ።

በመኸር አዝመራ ከ400 ሺህ ሄክታር በላይ ማሳ በማልማት ከ17 ሚሊዮን ኩንታል በላይ ምርት ለማግኘት እየተሰራ መሆኑን የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ምክትል ርዕሰ-መስተዳድርና የግብርና ቢሮ ኃላፊ አቶ ማስረሻ በላቸው ገለጹ። ‎ ‎በክልሉ በካፋ ዞን የአዲዮ እና በቤንች ሸኮ ዞን የጉራፈርዳ ወረዳ አርሶ-አደሮች ለተሻለ ውጤት እየተጉ እንደሚገኙ ተናግረዋል። ‎ ‎የክልል ምክትል ርዕሰ-መስተዳድርና የግብርና ቢሮ ኃላፊ አቶ…

Read More

የአከባቢው ህዝብ ለእንግዳ የሚሰጠውን ክብርና እንክብካቤ በጎበኘነው ተፈጥሮ ሀብት ላይ አረጋግጠናል ሲሉ ልዑኳን ቡድኖች ተናገሩ

የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልላዊ መንግስት የሸካ ዞን ማሻ ከተማ ህዝብ እንኳን ለሰው ልጅ ለተፈጥሮ ሀብት የሰጠው እንክብካቤ የሚደነቅ መሆኑን በጎበኙት ተፈጥሮ ሀብት ማረጋገጣቸውን 3ኛው ክልል ዓቀፍ የባህል ስፖርቶችና ባህል ፌስቲቫል ውድድር ልዑካን ቡድኖች ተናግረዋል። 3ኛው ክልል ዓቀፍ 21ኛው የባህል ስፖርቶችና 17ኛው ባህል ፌስቲቫል ተወዳዳሪ ልዑኳን ቡድኖች ከውድድሩ ጎን ለጎን በሸካ ዞን ማሻ ወረዳ የሚገኘውን…

Read More

የኑሮ ውድነት ፣ስራ ዕድል ፈጠራና ከተረጅነት ለመላቀቅ የተያዙ ግቦች በተሟላ መልኩ እንዲፈጸሙ የባለድርሻ ተቋማት ቅንጅት ሊጠናከር እንደሚገባ የብልጽግና ፓርቲ ምክትል ፕሬዝዳንትና የዋና ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ አደም ፋራህ ገለጹ

የብልጽግና ፓርቲ 2018 በጀት ዓመት የሩብ ዓመት አፈጻጸም ግምገማ መድረክ ዛሬም ቀጥሎ በመካሄድ ላይ ነው። በዛሬው መድረክም በፓርቲና በመንግሥት ቅንጅት የሚሰሩ ስራዎች አፈጻጸም ቀርቦ ውይይት እየተካሄደ ሲሆን የስራ ዕድል ፈጠራ ፣ኑሮ ውድነትን ለመቀነስ የተሰሩ ስራዎችና የተገኙ ውጤቶች እንዲሁም ከተረጅነት የመላቀቅ ግቦች የውይይቱ አጀንዳዎች ናቸው። የብልጽግና ፓርቲ ምክትል ፕሬዚዳንትና የዋና ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ አደም ፋራህ እንዳሉት፤…

Read More

3ኛዉ ዙር የግንባር ቀደም ግብር ከፋዮች የእውቅና እና ሽልማት መርሐ ግብር እየተካሄደ ነው

የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ክልል ርዕሰ መስተዳድር ኢንጂነር ነጋሽ ዋጌሾ (ዶ/ር) በተገኙበት 2017 በጀት ዓመት የ3ኛዉ ዙር የግንባር ቀደም ግብር ከፋዮች የእውቅና እና ሽልማት መርሐ ግብር በሚዛን አማን ከተማ እየተካሄደ ይገኛል። የክልሉ ገቢዎች ቢሮ ባዘጋጀው በዚሁ መረሐ ግብር በ2017 በጀት ዓመት ግብር ዘመን በክልሉ ለታክስ/ግብር ህግ ተገዥ ለሆኑ ግንባር ቀደም ግብር ከፋዮች እውቅና እና ሽልማት…

Read More

ለበጋ መስኖ ስንዴ የምርጥ ዘርና የማዳበሪያ አቅርቦት በስፋት እየተከናወነ ነው – ግብርና ሚኒስቴር

ለ2018 በጀት ዓመት የበጋ መስኖ ስንዴ ምርትና ምርታማነትን የሚያሳድጉ የምርጥ ዘርና የማዳበሪያ አቅርቦት በስፋት እየተከናወነ መሆኑን ግብርና ሚኒስቴር አስታውቋል። ሚኒስቴሩ ከ767 ሺህ ሄክታር በላይ መሬት በማረስ ከዚህ ውስጥም ከ359 ሺህ ሄከታር መሬት በላይ በዘር መሸፈኑን ገልጿል። የበጋ መስኖ ስንዴ ልማት የምግብ ዋስትናን ከማረጋገጥ ባለፈ የአርሶ አደሩን የስራ ባህል በመቀየር በዓመት ከሁለት ጊዜ በላይ እየተመረተ ይገኛል።…

Read More

በቦንጋ ከተማ አስተዳደር ለሰባተኛው ሀገራዊ ምርጫ የሚደረገው የአደባባይ ላይ የቅስቀሳ መርሃ ግብር ተጠናክሮ ቀጥሏል።

በዛሬው ዕለትም የኮሌጅ ፣ የሸታ እና የዩኒቨርሲቲ ቀጠና ነዋሪዎች አደባባይ ላይ በመውጣት ለብልፅግና ፓርቲ ያላቸውን ድጋፍ አሳይተዋል። በአደባባይ ድጋፍ ሰልፍ ላይ የተገኙት የቦንጋ ከተማ ከንቲባ ዶ/ር ተክለአብ ቡሎ ለፓርቲው ያላቸውን ድጋፍ ለማሳየት ለወጡ ነዋሪዎች ምስጋናቸውን በማቅረብ ሀገራችን ለረጅም ጊዜ በቁርሾ ፖለቲካ እና በብዙ ውጣ ውረዶች ውስጥ ማለፏን አስታውሰው አሁን ያለው ትውልድ በትከሻው የተጣለውን የሀገር ኃላፊነት…

Read More

በታክስ ማጭበርበር ወንጀል የተያዙ መዝገቦች ፈጣን እልባት እንዲያገኙ በየደረጃው የሚገኙ ፍትህ ተቋማት ትኩረት እንዲሰጡ ቢሮዉ አሳሰበ

​የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ገቢዎች ቢሮ የታክስ ማጭበርበር ወንጀልን ለመዋጋትና የህግ ማስከበር ስራን ለማጠናከር ያለመ የባለድርሻ አካላት የውይይት መድረክ በቦንጋ ከተማ አካሄደ። ​በመድረኩ ላይ የተሳተፉ ባለድርሻ አካላት የክልሉን የገቢ አሰባሰብ ስርዓት ለማጠናከርና የታክስ ማጭበርበርን ለመከላከል የበኩላቸውን ሚና ለመወጣት ዝግጁ መሆናቸውን አረጋግጠዋል። ተሳታፊዎቹ አክለውም ደረሰኝ በማበላለጥ፣ ደረሰኝ ባለመቁረጥና በተለያዩ መንገዶች የታክስ ስወራ በሚፈጽሙ የንግድ ተቋማት…

Read More

የ2016 የምርት ዘመን ክልላዊ የበጋ መስኖ ስንዴ ማስጀመሪያ መርሀግብር ተካሄደ።

የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል የ2016 የምርት ዘመን የበጋ መስኖ ስንዴ የማብሰሪያ መርሀግብር የክልል አመራሮች እና የባለድርሻ አካላት በተገኙበት በካፋ ዞን ገዋታ ወረዳ ተካሂዷል። የክልሉ የግብርና ምርምር ኢንስቲትዩት ከግብርና ቢሮ ጋር በመተባበር በወረዳው ሜዳቦ ቀበሌ በ50 ሄክታር ኩታ ገጠም ማሳ የመንግሥት የስራ ኃላፊዎች እና የአከባቢው አርሶደአሮች ጋር በመሆን የበጋ መስኖ ስንዴ እርሻን አብስረዋል። በክልሉ 7…

Read More

ርዕሰ መስተዳድር ኢንጅነር ነጋሽ ዋጌሾ (ዶ/ር) በቦንጋ ከተማ የሚከናወኑ የልማት ፕሮጀክቶችን በመጎብኘት የአፈጻጸም ክፍተቶች እንዲታረሙ አቅጣጫ አስቀምጠዋል።

የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ርዕሰ መስተዳድር ኢንጅነር ነጋሽ ዋጌሾ (ዶ/ር) በቦንጋ ከተማ እየተከናወኑ ያሉ የኮሪደር ልማት፣ የማረሚያ ተቋም እና የቦንጋ ዘመናዊ መናኸሪያ የግንባታ ሂደትን በዛሬው ዕለት ተዘዋውረው ተመልክተዋል። በክልሉ መንግሥት በከፍተኛ በጀት ግንባታው እየተከናወነ የሚገኘው የቦንጋ መናኸሪያ የመጀመሪያው ምዕራፍ የአስፋልት ንጣፍ ሥራ አሁን ላይ እየተገባደደ ሲሆን፣ በቅርብ ጊዜ ውስጥ ለአገልግሎት ክፍት እንደሚሆን ተገልጿል። ርዕሰ…

Read More