የከንቲባ ችሎት የህዝብ የመልካም አስተዳደር ችግሮችን በአጭር ጊዜ ውስጥ ለመፍታት ዓይነተኛ ሚና እንዳለው ተገለጸ።
የአውራዳ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ ችሎት የህዝብ የመልካም አስተዳደር ችግሮች ለመፍታት ትኩረት ሰጥቶ እየሰራ መሆኑን አስታወቀ ። የለውጡ መንግስት የህዝብን የመልካም አስተዳደር ችግሮች ለመፍታት ባስቀመጠው አቅጣጫ መሠረት በከተማችን የከንቲባ ችሎት በ2017 ዓ/ም ስራ መጀመሩን የአውራዳ ከተማ ከንቲባ አቶ ታረቀኝ ኃይሌ ተናግረዋል። የከንቲባ ችሎት የከተማ መሬት አገልግሎት አሰጣጥ፣ የፍትህ እጦት፣የመልካም አስተዳደር ችግር፣የመንግስት ተቋማት አገልግሎት አሰጣጥ እና ሌሎች…
