በግብርናው ዘርፍ በተለያዩ ፕሮግራሞችና ፕሮጀክቶች ድጋፍ የሚከናወኑ ተግባራት የግብርና ምርታማነት ለማሳደግ የሚኖረው ሚና ከፍተኛ በመሆኑ የተጀመሩ ሥራዎች ተጠናክሮ እንደሚቀጥሉ አቶ ማስረሻ በላቸው ገለጹ።
የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ግብርና ቢሮ SNV HORT LIFE 3 ፕሮግራም ጋር በመተባበር የአርሶ አደር የመስክ ትምህርት ቤት ተቋማዊ ማድረግ በሚያስችሉ ጉዳዮች ዙሪያ ከባለድርሻ አካላት ጋር በቦንጋ ከተማ ተወያይተዋል። በመድረኩም በፕሮግራሙ እስካሁን የተሰሩ ሥራዎችን ማጠናከር እና ቀጣይ መሻሻል በሚገቡ ጉዳዮች ላይ ከተሳታፊዎች ሀሳብ አስተያየቶች ተነስተው ሰፊ ውይይት ተደርጓል። የክልሉ ምክትል ርዕሰ መስተዳድር እና የግብርና…
