Trendings

የክልሉ የሥነ-ምግባርና ፀረ – ሙስና ኮሚሽን በሃብት ማሳወቅና ምዝገባ ሂደት ላይ ለካፋ ዞን ማዕከል የመንግስት ሰራተኞች ስልጠና ሰጠ ።

የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል የስነ-ምግባርና ፀረ – ሙስና ኮሚሽን ከአስር ቀን በኋላ ተግባራዊ የሚደረገውን የሃብት ማሳወቅና ምዝገባ ሂደት አስመልክቶ ከካፋ ዞን ማዕከል ለተወጣጡ መንግስት ሰራተኞች በቦንጋ ከተማ የግንዛቤ ስልጠና ሰጥቷል። በመድረኩ የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የኮሚሽኑ ምክትል ኮሚሽነር አቶ ዳግም ዳንኤል ሃብት ማሳወቅና ማስመዝገብ በመንግስት ተቋማት፡ በመንግስት የልማት ድርጅቶችና በህዝባዊ ድርጅቶች መካከል መልካም ስነ-ምግባርና እሴተቶች…

Read More

ጥራት ያለውን ቡና በማዘጋጀት ለማዕከላዊ ገበያ ለማቅረብ በትኩረት እየተሰራ እንደሚገኝ ተገለጸ።

የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ከፍተኛ መጠን ያለውን ቡና ለማዕከላዊ ገበያ በማቅረብ ከግምባር ቀደሞቹ ተርታ የሚመደብ ቡና አምራች አከባቢ ነው። በክልሉ ቤንች ሸኮ ዞን፣ ደቡብ ቤንች ወረዳ ቡና በስፋት እንደሚለማ የገለጹት የወረዳው ዋና አስተዳዳሪ አቶ ተሾመ ኪያስካ በዚህም የአምራች አርሶአደሮች ገቢ ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ መምጣቱን ተናግረዋል። የቡና ጥራት ለማስጠበቅ ተግባራዊ የኾነው የቡና ፓኬጅ ማሻሻያ…

Read More

ከስራ ዕድል ፈጠራ አኳያ የክልሉ መንግስት በሰጠው ልዩ ትኩረት ከባለድርሻ አካላት ጋር በመቀናጀት ውጤታማ ተግባራትን እያከናወነ እንደሚገኝ የስራና ክህሎት ቢሮ አስታወቀ።

የቢሮው ሀላፊ ዶ/ር ዐብይ አንዴሞ ቢሮው በክልሉ በ2018 በጀት አመት 10 ወራት ውስጥ የዜጎችኝ ተጠቃሚነት የሚያረጋግጡ ተግባራት ማከናወኑን ተናግረዋል። ሀላፊው አክለውም ከስራ ዕድል ፈጠራ አኳያ በግብርና፣በኢንዱስትሪና አገልግሎት ዘርፎች በአጠቃላይ ለ62 ሺ 72 ዜጎች የስራ ዕድል መፈጠሩንም አብራርተዋል። የቢሮው ምክትል ሀላፊና የስራ እድል ፈጠራና ኢንተርፕራይዝ ልማት ዘርፍ ሀላፊ አቶ ዳዊት ወንድሙ በበኩላቸው ቢሮው ከፋይናንስ አቅርቦት አንፃር…

Read More

የኢትዮጵያ የባህር ትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ 23 ነጥብ 46 ቢሊዮን ብር ገቢ አገኘ::

የኢትዮጵያ የባህር ትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ በበጀት ዓመቱ አጋማሽ 23 ነጥብ 46 ቢሊዮን ብር ገቢ ማግኘቱን አስታወቀ። የኢትዮጵያ የባህር ትራንስፖርትና ሎጅስቲክ በ2016 በጀት አመት አጋማሽ በሺፒንግ ዘርፍ ፣ በጭነት አስተላላፊነት ፣ በወደብና ተርሚናል አገልግሎት እንዲሁም በኮርፖሬት አገልግሎት ዘርፍ የተለያዩ ስራዎችን ማከናወኑን ገልጿል። በዚህም በመጀመሪያው ግማሽ ዓመት ከሚሰጡ አገልግሎቶችና ከሌሎች የገቢ ምንጮች 17 ነጥብ 23 ቢሊዮን ብር ለመሰብሰብ…

Read More

ሁለንተናዊ ብልጽግናን ለማረጋገጥ እንዲቻል ጤናው የተጠበቀ ማኅበረሰብ መፍጠር ወሳኝ መሆኑ ተገለጸ

የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ክልል ጤና ቢሮ የጤናና ጤና ነክ አገልግሎት ግብዓት ጥራት ቁጥጥር ባለሥልጣን የዓመቱን ዕቅድ አፈጻጸም በታርጫ ከተማ እየገመገመ ነው። በክልሉ ተርጫ ከተማ እየተካሄደ ባለው የዕቅድ አፈጻጸም ላይ በጤና ቢሮ የጤናና ጤና ነክ አገልግሎት ግብዓት ጥራት ቁጥጥር ባለሥልጣን ዋና ዳይሬክተር አቶ ሙሉቀን አሰፋ እንደገለጹት በ2016 በጀት ዓመት በክልሉ የሚገኙ ነዋሪዎችን ጤና ለማስጠበቅ የጋራ…

Read More

ቆይታ ከእኛ ጋር

የትራንስፖርት አገልግሎት ማህበራዊ፣ኢኮኖሚያዊና አስተዳደራዊ ጉዳዮች እንዲሳለጡ ከፍተኛ ሚና ከሚጫወቱ ዘርፎች አንዱና ዋነኛው መሆኑን በዕለት ተዕለት እንቅስቃሴያችን ማረጋገጥ እንችላለን። የትራንስፖርትና መንገድ ልማት ዘርፍ በአስፈላጊነቱ ልክ በተዋንያኖቹ ምክንያት በሚፈጠሩ ህገ ወጥ አሰራሮች በዜጎች ላይ የኑሮ ጫና ከመፍጠሩም በላይ ለመልካም አስተዳደር ጥያቄዎችም ሰፊውን ድርሻ እንደሚወስድ አጠያያቂ አይደለም።ከቅርብ ጊዜ ወድህ በዓለም አቀፍ ገበያ ጫና የነዳጅ እና መለዋወጫ እቃዎች ዋጋ…

Read More

ብዝሃ ዘርፍ ትብብርን በተመለከተ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አቢይ አህመድ የሰጡት ማብራሪያ

የኢትዮጵያ ኢኮኖሚ ከግብርና መር ወደ ብዝሃ ዘርፍ እንዲሸጋገር የተነደፈው ፖሊሲ በእጅጉ ውጤታማ ሆኗል። መንግስት ከህዝብ ጋር ተሳስሮ ልማት እንዲያመጣ ግልጽ አቅጣጫ የተቀመጠውም ከለውጡ ወዲህ ነው። ለአብነትም መንግስትና ህዝብ ተሳስረው በአረንጓዴ አሻራ አማካኝነት 48 ቢሊዮን ችግኞችን መትከል ችለዋል። ለዚህ ስኬት ደግሞ ከ25 ሚሊዮን በላይ ኢትዮጵያዊያን ሳይታክቱ በነጻ በየ ዓመቱ ወጥተው ችግኞችን መትከል ችለዋል። ይህም የመንግስትና ህዝብ…

Read More

ሰላምን በማጽናት ልማትን ለማረጋገጥ መንግስትና ህዝብ እጅ ለእጅ ተያይዘው መስራት እንዳለባቸው ተገለጸ።

በደብረ ብርሃን ከተማ” የጉባ ብስራቶች፣ የመደመር መንግስት ትሩፋቶች” በሚል መሪ መልዕክት ሕዝባዊ ውይይት እየተካሄደ ነው። በውይይቱ የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድር እና ግብርና ቢሮ ኃላፊ እና የብልጽግና ፓርቲ ሥራ አስፈጻሚ የተከበሩ ማስረሻ በላቸው፣ና የሸገር ከተማ ከንቲባና የብልጽግና ፓርቲ ሥራ አስፈጻሚ ተሾመ አዱኛ (ዶ/ር) ጨምሮ የከተማው ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች ተገኝተዋል። ‎የደብረ ብርሃን ከተማ…

Read More

በጥናትና ምርምር የተለዩና የተሻሻሉ ዝርያዎችን በማስፋፋት የአርሶአደሩን ተጠቃሚነት ማሳደግ ይገባል ፡፡ አቶ ማስረሻ በላቸው

በጥናትና ምርምር ስራዎች የግብርና ምርታማነት ማነቆዎችን በመፍታት የአርሶ አደሩን ተጠቃሚነት ማሳደግ እንደሚገባ ተገልጿል፡፡ የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ግብርና ምርምር ኢንስቲትዩት በምግብ ሥርዓት ማጠናከሪያ ፕሮግራም ድጋፍ በዳሰሳ ጥናት በተለዩ የግብርና ልማት ማነቆዎችና በቀጣይ አቅጣጫ ዙርያ የባለድርሻ አካላት የውይይት መድረክ በቦንጋ ከተማ አካሂዷል። በምክክር መድረኩ የተገኙት የክልሉ ምክትል ርዕሰ መስተዳድር እና የግብርና ቢሮ ኃላፊ አቶ ማስረሻ…

Read More