Trendings

#ካንካርና_ኩችጓ

ባህል የአንድ ብሔረሰብ ማንነት መገለጫው፤ ትልቅ እሴቱ ነው። ባህልን ማልማት፣ ማሳደግ ለትውልድ ማሸጋገር ደግሞ የአሁኑ ትውልድ ትልቅ አደራው ነው። ይህ ትልቅ አደራ ሳይሸረፍ፣ሳይበረዝ የጥንት ይዘቱን ጠብቆ እንዲለማ ማድረግም ያስፈልጋል። በክልላችን በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ከሚገኙ ብሔረሰቦች አንዱ የፃራ ብሔረሰብ ነው ። ብሔረሰቡ የራሱ የሆኑ ባህላዊ እሴቶች አሉት ።ከእነዚህ እሴቶች ውስጥ አንዱ ባህላዊ አለባበስና አጋጌጥ ተጠቃሽ ነው…

Read More

ኢንጂነር ነጋሽ ዋጌሾ (ዶ/ር ) የክልሉን የዲጂታል ትራንስፎርሜሽን ጉዞ ለማፋጠን ያለመ ዉይይት ከኢትዮ-ቴሌኮም ጋር አካሄዱ

ውይይቱ የመሶብ ማዕከላትን፣ የዲጂታል መታወቂያንና የኢ-ቲኬት አገልግሎትን እንዲሁም የፋይዳና የ5 ሚሊየን ኮደርስ ለማስፋፋት ትኩረት አድርጓል። የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ርዕሰ መስተዳድር ክቡር ዶ/ር ኢንጂነር ነጋሽ ዋጌሾ ከኢትዮ-ቴሌኮም ዋና መሥሪያ ቤትና ከጂማ ዲስትሪክት ከመጡ ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎችና ባለሙያዎች ጋር በጽህፈት ቤታቸው ተወያይተዋል። ውይይቱ የክልሉን የዲጂታል ሽግግር እውን ለማድረግ በቀጣይ በጋራ ሊሰሩ በሚገባቸው ወሳኝ ጉዳዮች ላይ…

Read More

የመጋቢት ቃል ኪዳን – እንደ ታሰሩት እንጨቶች የማይበገረው አንድነታችን!

በጥንት ዘመን፣ አንድ ስመ-ጥሩ አንጥረኛ ይኖር ነበር። ይህ አንጥረኛ ለሀገሩ ጋሻ እና ጦር በመቅረጽ ይታወቃል። አንድ ቀን ጠላት በሀገሪቱ የሚሰነዝረው ጥቃት ሁሌ ስለሚከሽፍበት የሀገሪቱ ጥንካሬ ከአንጥረኛው አሠራር ጭምር ነው ብሎ አሰበና “ጋሻውን መስበር ካልቻልን፣ ጋሻውን የያዘውን እጅ እንቁረጥ፤ ጦሩን መመከት ካቃተን፣ ጦሩን የሚወረውረውን ትከሻ እርስ በእርሱ እናጋጭ” የሚል የውስጥ በትር ሰነዘረ። አንጥረኛው ይህንን ሰማና የሀገሩን…

Read More

“ጉልፋ”-የናይዎች ጥበብ

ናይዎች በክልላችን ከሚገኙ የውብ ባህላዊ እሴቶች ባለቤት ከሆኑ ህዝቦች መካከል ይጠቀሳሉ። ባህላቸው ውበታቸው፣ ህይወታቸውም ነው።ናይዎች በፍቅር ሲጠጓቸው ያላቸውን ሁሉ ይሰጣሉ።የማስመሰል ዝምድናን አያውቁም። ናይዎች ደስታቸውን በተለያየ መንገድ ይገልፃሉ። በደስታ ጊዜ ስሜታቸውን የሚገልፁበት መሳሪያ የትንፋሽ መሳሪያ “ጉልፋ” ይባላል። “ጉልፋ” ከቀርከሀ የሚሰራ ነው። በአንደ ጊዜ የትንፋሽ ድምፅ የሚያወጣ “ጉልፋ” በቁጥር አምስት ሲሆን አንዱ ቢጎል መሳሪያዉ መልእክት ያለዉን ድምጽ…

Read More

“ማሽቃሮ” የካፋ ህዝብ ማህበራዊ መስተጋብር የሚንፀባረቅበት ታላቅ በዓል ስለሆነ እንደ አባቶቻችን ተንከባክበን እናቆየዋለን:- የበዓሉ ተሳታፊ ወጣቶች

የካፈቾ ብሔር ዘመን መለወጫ “ማሽቃሮ” በተለያዩ ትይንቶች በቦንግ ሻምበቶ ተከብሯል። በዓሉን ሲያከብሩ የነበሩት ወጣቶች ማሽቃሮ አዝመራው አልቆ አዲስ ብርሃን ጮራ የሚናይበት ተናፋቂ በዓል ነው ብለዋል። ማሽቃሮ በካፈቾ ዘንድ ልዩ ስፍራ ያለውና በጉጉት የሚጠበቅ ዓመታዊ ትይንት በዓል ነው ያለው ወጣት ሙሉቀን ካሳሁን ይህ ዕሴት በቀላሉ እዚህ አልደረሰምና እኛም በባለቤትነት ስሜት የሚንኮራበትን ባህል በመለማመድ ለትውልድ እናሸጋግራለን ብለዋል።…

Read More

የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላት ለጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ካቀረቧቸው ጥያቄዎች እና አስተያየቶች መካከል:-

በኢትዮጵያ ግዙፍ የልማት ፕሮጀክቶችን በመገንባት የህዝብ ጥያቄን ለመፍታት እና የሀገሪቱን ብልጽግና ለማረጋገጥ የሚሰራው ስራ የሚደነቅ ነው ዘላቂ የሰላም ግንባታን ከማጠናከር አንጻር ምን አቅጣጫ ተይዟል ? በሀገሪቱ የሚስተዋለውን ከፍተኛ የዋጋ ንረት እና የኑሮ ውድነት ለማቃለል መንግስት የያዘው አቅጣጫ ካለ ቢብራራ 7ኛውን ሀገራዊ ምርጫ የተሳካ ለማድረግ የተፈጠሩ አስቻይ ሁኔተዎች ምንድናቸው እንዲሁም የምርጫውን ሂደት ለማደናቀፍ የሚንቀሳቀሱ ሀይሎችን ለመግታት…

Read More

ኢትዮጵያ ጫናዎቹን ወደ ዕድል በመቀየር የሕዳሴ ግድብን አሁን ላለበት ደረጃ አብቅታለች፦ አምባሳደር ኢብራሒም ኢድሪስ

ኢትዮጵያ ጫናዎቹን ወደ ዕድል በመቀየር ታላቁ ሕዳሴ ግድብን አሁን ላለበት ደረጃ አብቅታለች ሲሉ አምባሳደር ኢብራሒም ኢድሪስ ገልጸዋል። የድንበርና ድንበር ተሻጋሪ ሐብት ጉዳዮች ተመራማሪ በዘርፉ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አማካሪ አምባሳደር ኢብራሒም ኢድሪስ ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብን በተመለከተ በዛሬው የኢቲቪ አዲስ ቀን “የሀገር ጉዳይ” መሰናዶ ላይ ሀሳባቸውን አጋርተዋል። የግድቡ ግንባታ ከመጀመሩ በፊትም ሆነ ከተጀመረ በኋላ ከጎረቤት ሀገራትና…

Read More

የቴፒ አጠቃላይ ሆስፒታል አገልግሎት አሰጣጥ እየተሻሻለ መምጣቱ ተገለጸ

በሸካ ዞን የቴፒ አጠቃላይ ሆስፒታል የአገልግሎት አሰጣጥን ይበልጥ ለማሻሻል የሁሉም ማህበረሰብ ድጋፍ እንደሚያስፈልግ ተገልጿል። የሆስፒታሉ አገልግሎት አሰጣጥ እየተሻሻለ መምጣቱ የተገለፀ ሲሆን በዘርፉ የሚስተዋሉ ችግሮችን ሁሉም ባለድርሻ አካላት እንዲፈቱም ተጠይቋል። የቴፒ አጠቃላይ ሆስፒታል ስራ አስኪያጅ አቶ አስታወሰኝ አዴሎ እንደገለፁት ሆስፒታሉ ከአካባቢው ነዋሪዎች ባሻገር ከአጎራባች ክልሎች እና ዞኖች ለሚመጡ የማህበረሰብ ክፍሎች አገልግሎት የሚሰጥ ከመሆኑ ጋር ተያይዞ በቀን…

Read More

የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልልን ምን ያህል ያውቃሉ?

ባለፉት ተከታታይ ወራት ‘’የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልልን ምን ያህል ያውቃሉ?’’ በሚል አምድ ሥር አጠቃላይ የክልላችንን ገጽታ፣ የምዕራብ ኦሞ፣ የካፋ፣ የዳዉሮ፣ የቤንች ሸኮ እና የሸካ ዞኖችን አጠቃላይ ገጽታን የሚያሳዩ፤ የካፋ ባህላዊ ዱሞ ስርዓትና የዳውሮ ዱቡሻ ስርዓትን የቃኙ ጽሁፎችን እንደየቅደምተከተላቸው ለውድ አንባቢያን አጋርተናል፡፡ አሁን ደግሞ የኮንታ ብሔረሰብ ዘመን መለወጫ በዓል ህንግጫን እንቃኛለን፡፡ መልካም ንባብ!የኮንታ ብሔረሰብ በርካታ…

Read More

የቤንች ሸኮ ዞን ብልጽግና ፓርቲ የ2018 በጀት ዓመት የመጀመሪያ ግማሽ ዓመት የአመራር ግምገማና ምዘና መድረክ መካሄድ ጀምሯል።

በመድረኩ ላይ የዞኑን ወቅታዊ የልማትና የመልካም አስተዳደር ስራዎች በመፈተሽ፣ የአመራሩን ቁመና የማጥራት ስራ ትኩረት እንደሚሰጠው ተገልጿል። በመድረኩ ላይ ተገኝተው ንግግር ያደረጉት የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል መንግስት ዋና አፈ ጉባኤ ክቡር አቶ ወንድሙ ኩርታ ዞኑ በክልል ደረጃ የተሻለ አፈፃፀም እያስመዘገበ ያለ ዞን መሆኑን ጠቅሰዋል። ይሁን እንጂ የተመዘገቡ ስኬቶችን ለማስቀጠልና ህዝባዊ አገልጋይነትን ለማረጋገጥ አመራሩን በሦስት ዋና…

Read More