የሚዛን ግብርና ቴክኒክ ሙያ ትምህርት ስልጠና ኮሌጅ የራሱን ገቢ አመንጭቶ ራሱን እያስተዳደረ የተሻለ ደረጃ ላይ እንዲደርስ እየተሰራ መሆኑ ተገለፀ::
የቴክኖሎጂ ብዜትና ሽግግር ስራም ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ተጠቁሟል፡፡ የኮሌጁ ዲን አቶ ካሳሁን ናይክን እንደገለፁት ኮሌጁ የራሱን ገቢ አመንጭቶ የተሻለ ደረጃ ላይ እንዲደርስ ከስራና ክህሎት ሚኒስተር በተቀመጠው አቅጣጫ መሠረት እየተሰራ ነው፡፡ ኮሌጁ ከተመሠረተ ጊዜ አንስቶ በመማር ማስተማር፣ በቴክኖሎጂ ብዜትና ሽግግር ላይ በርካታ ተግባራትን ሲያከናውን መቆየቱን አቶ ካሳሁን አስታውሰው አሁን መሬት ላይ ያሉት ሀብቶችን በማዘመን ኮሌጁ የውስጥ ገቢውን…
