ጠ/ሚ ዐቢይ (ዶ/ር) ለዶናልድ ትራምፕ የእንኳን ደስ አለዎት መልዕክት አስተላለፉ
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ዶናልድ ትራምፕ የአሜሪካ ፕሬዚዳንት ሆነው በመመረጣቸው የእንኳን ደስ አለዎት መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡ ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባስተላለፉት መልዕክት÷በቀጣይ የሁለቱን ሀገራት ግንኙነት ለማጠናከር በትብብር እንደሚሰሩ ገልጸዋል ሲል ኤፍቢሲ ዘግቧል
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ዶናልድ ትራምፕ የአሜሪካ ፕሬዚዳንት ሆነው በመመረጣቸው የእንኳን ደስ አለዎት መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡ ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባስተላለፉት መልዕክት÷በቀጣይ የሁለቱን ሀገራት ግንኙነት ለማጠናከር በትብብር እንደሚሰሩ ገልጸዋል ሲል ኤፍቢሲ ዘግቧል
በቤንች ሸኮ ዞን “በመደመር መንግስት እይታ ለዘርፎች እምርታ” የመካከለኛ አመራሮች የስልጠና መድረክ ማጠቃለያ እየተካሄደ ይገኛል። ከህዳር 22 እስከ 30/2018 በዞን ማዕከል እየተካሄደ የሚገኘው የ3ኛ ዙር የመካከለኛ አመራሮች የስልጠና መድረክ ማጠቃለያ መርሀ ግብር እየተካሄደ ይገኛል። የቤንች ሸኮ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ ሀብታሙ ካፍትን የስልጠና መድረኩን ሲያጠቃልሉ እንደተናገሩት በሀሉም ዘርፎች እየተመዘገቡ የሚገኙ ውጤቶችን ከፓርቲው እሳቤ መነሻ በማድረግ…
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) “በሁሉም አካባቢ የሚኖረውን ህዝባችንን ፈተናዎች እና ፍላጎቶች ማዳመጥ ቀዳሚ ተግባራችን ነው” ሲሉ ገለጹ። ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማህበራዊ ትስስር ገፃቸው ባሰፈሩት ጽሁፍ ፤ከደቡብ፣ ደቡብ ምዕራብ፣ ሲዳማ እና ማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልሎች ከተወጣጡ ተወካዮች ጋር ውይይት ማድረጋቸውን ጠቁመዋል። በውይይቱም ተወካዮች በልማት ጉዳዮች ላይ አስተያየቶቻቸውን እና ጥያቄዎቻቸውን ማቅረባቸው የተገለጸ ሲሆን፤ ጠቅላይ ሚኒስትሩ የጋራ ግብ ላይ…
የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል መንገዶች ባለስልጣን ዋና መስሪያ ቤት እየተሰሩ ያሉ የመንገድ ጥገናና ድልድይ ፕሮጀክቶች ያሉበት ደረጃ ገምግመው ቀጣይ በሚጠናቀቁበት ጉዳዮች ላይ ከአማካሪዎች፣ ተቋራጮችና ባለድርሻ አካላት ጋር መክረዋል። በ2017 በጀት ዓመት በግልፅ ጨረታ አሸንፎ ወደ ስራ የገቡት አራት የስራ ተቋራጮች እና ሁለት አማካሪ ድርጅቶች እየተሰሩ ያሉ የኮቾ፣ኡሜ እና መንሳ ድልድዮች እንዲሁም ዳካ-ሳይለም ሎት 2…
በዛሬው ዕለት ፍትህ ሚኒስቴር ባዘጋጀው አህጉር አቀፍ ባህላዊ ግጭት አፈታት ኮንፍረንስ ላይ በሀገር ደረጃ ከተመረጡ አራት ክልሎች አንዱ በመሆን የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልልን በመወከል የካፋ ባህላዊ የግጭት አፈታት ስርዓት (Qaabbitino) ተመርጧል። በዚህም በካፋ ዞን ሺሾእንዴ ከተማ ከቀጠና 1-4 የተመረጡ የባህላዊ ፍርድ ቤት ዳኞች( ሽማግሌዎች) አለመግባባቶችን እንዴት በባህላዊ መንገድ እንደሚፈቱ ለታዳሚዎች አሳይቷል ሲል የካፋ ዞን…
የሚኒስትሮች ምክር ቤት በዛሬው ዕለት ባካሄደው 42ኛ መደበኛ ስብሰባ በተለያዩ ጉዳዮች ላይ ተወያይቶ ውሳኔ አሳለፈ፡፡ ውሳኔዎቹ እንደሚከተለው ቀርበዋል፡- በቅድሚያ ምክር ቤቱ የተወያየው የኢትዮጵያ የአደጋ ሥጋት ሥራ አመራር ረቂቅ አዋጅ ላይ ነው፡፡ አዋጁ በተቋሙ የተጀመረውን የሪፎርም ስርዓት ወደ ተግባር በመለወጥ በኢትዮጵያ የህዝቡን የእርስ በእርስ መረዳዳት ባህል የማጎልበትና ተረጂነትን በዘላቂነት በሀገር አቅም መወጣትን ማዕከል በማድረግ የአደጋ ጉዳት…
ሌዊ ሪዞርት በቦንጋ ከተማ ያስገነባው ዘመናዊ ሆቴልና ሪዞርት የክልሉን የኮንፈረንስ ቱሪዝም የሚያሳልጥ መሆኑን ነው የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድርና የግብርና ቢሮ ኃላፊ አቶ ማስረሻ በላቸው በምረቃው ስነ-ስርዓት ወቅት የገለጹት። ክልሉ ለሆቴልና ኢኮ-ቱሪዝም እንቨስትመንት ምቹ አከባቢ መሆኑን የገለጹት አቶ ማስረሻ የክልሉን እምቅ የቱሪዝም ሀብት ለመጠቀም በአግልግሎት ዘርፍ የአልሚዎች ተሳትፎ ተጠናክሮ መቀጠል አለበት ብለዋል።…
ከሚያዝያ 08/2018 ዓ.ም ጀምሮ ለተከታታይ 8 ቀናት ሲካሄድ የቆየዉ የ2018 ዓ.ም የሸካ ዞን እግር ኳስ ክለቦች ሻምፒዮና ዉድድር ፍፃሜውን አግኝቷል ። በዉድድሩ መዝጊያ መርሃ ግብር ላይ ተገኝተዉ ንግግር ያደረጉት የሸካ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ አበበ ማሞ ስፖርት በስነ ምግባር የታነፀ፣ በአካል የዳበረ ፣በአዕምሮ የበለፀገ፣ በህብረ ብሄራዊ ኢትዮጵያዊነት የሚያምን ዜጋን ለመፍጠር ከፍተኛ ድርሻ እንዳለው ገልፀዉ ለዉድድሩ…