የክልሉ ኦዲት አስመላሽ ግብረሃይል በየጊዜው በሚያካሂዳቸው ግምገማዎች እና በሚያስቀምጣቸው አቅጣጫዎች በኦዲት ግኝት ላይ ውጤቶች እየተመዘገቡ ነዉ ፦ የተከበሩ ዋና -አፈጉባኤ አቶ ወንድሙ ኩርታ
የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ፋይናንስ ቢሮ እና የክልሉ ምክር ቤት በጋራ አዘጋጅነት የኦዲት አስመላሽ ግብረሃይል እና ባለድርሻ አካላት ጋር የኦዲት በጀት አፈጻጸም በአመያ ከተማ እየገመገመ ነዉ። የክልሉ ምክር ቤት ዋና አፈ-ጉባኤ የተከበሩ አቶ ወንድሙ ኩርታ የአፈጻጸም ግምገማውን በንግግር በከፈቱበት ወቅት ፣የክልሉ ኦዲት አስመላሽ ግብረሃይል አጠቃላይ 14 አባላትን ያቀፈና በክልሉ ምክር ቤት አስተባባሪነት የኦዲት ግኝት…
