በሸካ ዞን ከ2017 ዓ.ም ጀምሮ በትኩረት በሚፈፀሙ ተግባራት ላይ ያተኮረ ውይይት በቴፒ ከተማ እየተካሄደ ይገኛል።
በዞኑ ከ2017 ዓ.ም ጀምሮ በኢኮኖሚ፣በማህበራዊ፣ በከተማ ልማት እንዲሁም በፖለቲካና ህዝብ ግንኙነት ዘርፎች በልዩ ትኩረት በሚፈፀሙ ተግባራት ዙሪያ ስትራቴጂካዊ ዕቅድ ቀርቦ ውይይት እየተካሄደ ነው። ውጤታማ ተግባራትን በመፈፀም የህብረተሰቡን እርካታ ለማረጋገጥ ብሎም የዞኑን ልማትና እድገት ለማፋጠን በየደረጃው የሚገኙ አመራሮችና ባለድርሻ አካላት ተሳትፎና ርብርብ ወሳኝ መሆኑም ተጠቁሟል። ከተማ ልማት፣ግብርና፣ገቢ አሰባሰብ፣ትምህርትና ጤና ዘርፍ ላይ እመርታ ማስመዝገብ ከርብርብ ማዕከላት ዋነኞቹ…
