የድሮ አባቶቻችን ደምና የህይወት መስዋዕትነት በመክፈል ጠብቆ ያቆዩልንን ሰንደቅ አላማ የአሁኑ ትውልድ ጠብቆ የማስቀጠል አደራ እንዳለበት ተገለጸ
ዘንድሮ ለ18ኛው ጊዜ የሚከበረው የኢትዮጵያ የሰንደቅ ዓላማ ቀን በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል በቦንጋ ከተማ በፓናል ውይይት እና በተለያዩ ስነስርአቶች እየተከበረ ነው ቀኑ”ሠንደቅ ዓላማችን ለኢትዮጵያ ታላቅ የከፍታ ዘመን ብሥራት፣ ለብሔራዊ አንድነታችን፣ ለሉዓላዊነታችንና ለኢትዮጵያ ሕዳሴ!”በሚል መሪ ቃል ነው የተከበረ የሚገኘው። በስንደቅ ዓላማ ቀኑ ተገኝተው ንግግር ያደረጉት የካፋ ዞን ምክር ቤት ዋና አፈጉባኤ አቶ ግርማ ደፋር አንድ…
