በጎነትን ለማስረጽ እና የአብሮነት እሴቶችን ለማጎልበት የበጎ ፈቃደኛ ወጣቶች ሚና ከፍተኛ ነው ሲሉ የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል ሴቶች ህፃናት እና ወጣቶች ቢሮ ኃላፊ ወ/ሮ ገነት መኩሪያ ገለፁ።
የ2016 የወሰን ተሻጋሪ የወጣቶች በጎ ፈቃድ አገልገሎት ተሳታፊዎች በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ዳውሮ ዞን የተለያዩ በጎ ተግባራትን አከናውነዋል ። በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል መንግስት ሴቶች ህፃናት እና ወጣቶች ቢሮ ኃላፊ ወ/ሮ ገነት መኩሪያ እንደገለፁት ወሰን ተሻጋሪ የክረምት ወራት በጎ ፈቃደኛ ወጣቶች ሠላምን አስተማማኝና ዘላቂ ለማድረግ እየተከናወኑ ያሉ ተግባራትን ውጤታማ ለማድረግ ሚናቸው የጎላ ነው…
