ኮሚሽኑ የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል አጀንዳዎችን በይፋ ተረከበ
የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ከጥቅምት 24/2017 ዓ.ም ጀምሮ በሁለት ምዕራፎች ሲያከናውን የነበረውን የአጀንዳ ማሰባሰብ የምክክር መድረክ ዛሬ አጠናቋል። በሂደቱም በክልሉ የሚገኙ የተለያዩ ባለድርሻ አካላት በአጀንዳ ሀሳቦቻቸው ላይ ውይይት ሲያደርጉ ቆይተው አጀንዳዎቻቸውን ለይተው ለኮሚሽኑ አስረክበዋል፡፡ ኮሚሽኑ በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል በቦንጋ ከተማ ባከናወነው የአጀንዳ ማሰባሰብ የምክክር መድረክ ከክልሉ ሁሉም መዋቅሮች…
