በቴፒ የተከፈተው የምርት ጥራትና ሰርቲፊኬሽን ማዕከል የንግድ እንቅስቃሴውን እያቀላጠፈ መሆኑ ተገለጠ
በኢትዮጵያ ቡናና ሻይ ባለሥልጣን ስር የሚገኘው የቴፒ ምርት ጥራትና ሰርቲፊኬሽን ማዕከል አገልግሎት መጀመር በአካባቢው ለሚገኙ አምራቾች፣ ላኪዎችና ሥራ አጥ ወጣቶች ዘርፈ ብዙ ጥቅም እያስገኘ መሆኑ ተገለጠ። ማዕከሉ በተለይም በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ በሸካ ዞን ና በጋምቤላ ክልሎች የሚመረተው ቡና የራሱ መለያ ኖሮት ለገበያ እንዲቀርብ ምቹ ሁኔታ መፍጠሩ ተመላክቷል። የቴፒ ምርት ጥራት ምርመራና ሰርተፊኬሽን ማዕከል ሥራ ከጀመረ…
