Trendings

በከተማው የንጹህ መጠጥ ውሃ አቅርቦት ለማሻሻል በተሰጠው ትኩረት አዎንታዊ ለውጥ መመዝገቡ ተገለጸ

በዳውሮ ዞን፣ ታርጫ ከተማ የሚስተዋለውን ስር የሰደደ የንጹህ መጠጥ ውሃ አቅርቦት ለማሻሻል የባለድርሻ አካላት በሰጡት ትኩረት አውንታዊ ለውጥ መመዝገቡን የከተማ አስተዳደሩ አስታወቀ። የታርጫ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አቶ ዳዊት ወንድሙ፥ የዞኑ ዋና ከተማና የክልሉ ብዝሀ ማዕከል በሆነችሁ የታርጫ ከተማ የሚስተዋለውን የንጹህ መጠጥ ውሃ አቅርቦት በዘላቂነት ለማሻሻል የክልሉ መንግሥት ሌሎች የባለድርሻ አካላትን በማሳተፍ ባደረገው ርብርብ አሁን ላይ…

Read More

ለመላው የክርስትና እምነት ተከታዮች እንኳን ለጥምቀት በዓል በሰላም አደረሳችሁ።

ጥምቀት ኢትዮጵያ ለዓለም ያበረከተችው የአደባባይ የወል በዓል ነው። በዓሉ ከሃይማኖታዊ በዓልነት ባሻገር የሚታይ ለዓለም በማይዳሰስ ቅርስነት የተበረከተ ሀብታችን ነው፡፡ የበዓሉ መሠረት ሃይማኖታዊ ነው፡፡ ኢትዮጵያውያን ደግሞ ሃይማኖታዊ መሠረቱን እንደያዘ ባህላዊ እሴት እንዲኖረዉ ጭምር አድርገውታል፡፡ በዓሉ በየዓመቱ ሲከበር ከክርስትና ሃይማኖት ተከታዮች ባሻገር መላው ሕዝብ የሚታደምበት የዐደባባይ የወል በዓል ተደርጓል፡፡ ኢትዮጵያ ለዓለም ሕዝብ ያበረከተችው የማይዳሰስ ቅርስ ኾኖ መመዝገቡም…

Read More

የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ብልፅግና ፓርቲ ቅ/ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ፍቅሬ አማን ለሸኮ ብሔረሰብ የዘመን መለወጫ” ቲካሻ ቤንጊ “በዓልን የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላልፈዋል።

“ቲካሻ ቤንጊ” ከሸኮ ብሄረሰብ ቱባ ባህላዊና ታሪካዊ ክዋኔዎች ዉስጥ አንዱ ሲሆን ከአሮጌው አመት ወደ አዲሱ ዓመት ህዝቡን፣ ቤተሰቡን፣ ልጆቹን፣ እርሻውን፣ ከብቶቹንና ቀየውን በሠላም ጠብቆ ላቆየው ፈጣሪ ምስጋና የሚያቀርብበት በዓል ነው። በሌላ ጎኑ ለቀጣይ ዓመት በህዝባችን ላይ የሚመጣ ቸነፈር ፈጣሪ ይመልስ፣ ልጆች በሰላም ወጥተው ይግቡ፣ የተወለዱት ይደጉ፣ የተዘራው እህል ፍሬ ያፍራ፣ የተተከለው ተክል ስር ይያዝ፣ ምድሪቱ…

Read More

ርዕሰ መስተዳድር ኢንጂነር ነጋሽ ዋጌሾ (ዶ/ር) በተገኙበት የታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ ግንባታ መጠናቀቁን አስመልክቶ ህዝባዊ ሰልፍ እየተካሄደ ነው

የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ርዕሰ መስተዳድር ኢንጂነር ነጋሽ ዋጌሾ (ዶ/ር)ን ጨምሮ ሌሎች የክልሉ ከፍተኛ የመንግስት የሥራ ኃላፊዎች በተገኙበት የታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ ግንባታ መጠናቀቁን በማስመልከት ህዝባዊ ሰልፍ በቦንጋ ከተማ በመካሄድ ላይ ይገኛል። በኅብረት ችለናል’ በሚል መሪ ሐሳብ በቦንጋ ከተማ እየተካሄደ በሚገኘው የድጋፍ ሰልፍ ከክልሉ ከሁሉም ዞኖች ከተለያዩ አደረጃጀቶች የተወጣጡ የህብረተሰብ ክፍሎች የደስታ ስሜታቸውን በተለያዩ…

Read More

ወጣቶች ለሀገረ መንግስት እና ለሰላም እሴት ግንባታ ሚናቸውን በተገቢው ሊወጡ እንደሚገባ ተገለጸ

በካፋ፣ ሸካ እና በቤንች ሸኮ ዞኖች የብልጽግና ፓርቲ የወጣቶች ክንፍ ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤት ” ሀገሬን እገነባለሁ ኃላፊነቴን እወጣለሁ ” በሚል መሪ ቃል ዞን አቀፍ የወጣቶች ውይይት ተካሂዷል። መድረኮቹ ወጣቶች በማህበራዊ፣ በኢኮኖሚና በፖለቲካ ሁኔታዎች ላይ ግልፅ ግንዛቤ እና የጋራ አረዳድ በመፍጠር የሚጠበቅባቸውን ሚና እንዲወጡ ዓላማ ያደረገ ነው። ሀገራዊ ለውጡ እንደ ሁሉም የሀገራችን የህብረተሰብ ክፍሎች ወጣቶችን ተጠቃሚ…

Read More

ዞናዊ የሰብዓዊ ድጋፍን በራስ አቅም ለመፈፀምና የምግብ ዋስትናን ለማረጋገጥ የሚያስችል ዞናዊ የንቅናቄ መድረክ በሚዛን አማን ተካሄደ።

በቀጣይም 8700 ኩንታል ለስትራቴጂክ የምግብ ሰብል መጠባበቂያ ክምችት ከ240 ሄክታር በላይ መሬት ላይ እንደሚመረትም በንቅናቄ መድረኩ ተገልጿል። የቤንች ሸኮ ዞን ብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ ደግፌ ኩድን መድረኩን በንግግር ሲከፍቱ እንደተናገሩት እንደ ሀገር ተረጂነትን ማስቀረት የሀገር ሉአላዊነትና ክብርን ማስጠበቅ ነው ብለዋል። መንግስትም ተረጂነትና ልመናን የሚፈፀየፍ ትውልድና ሀገር ለመፍጠር በገጠርና በከተማ የምግብ ዋስትናን ለማረጋገጥ…

Read More

የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ምክር ቤት 6ኛ ዙር 5ኛ ዓመት የሥራ ዘመን 9ኛ መደበኛ ጉባኤ በታርጫ ከተማ እያካሄደ ይገኛል።

በጉባኤው የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ኢንጂነር ነጋሽ ዋጌሾ (ዶ/ር) የመንግስታቸውን የ2018 በጀት ዓመት የስድስት ወራት የማህበራዊ ዘርፍ ዕቅድ አፈጻጸም ሪፖርት ለክልሉ ምክር ቤት እያቀረቡ ይገኛሉ። ባለፉት ስድስት በትምህርት ዘርፍ ”ትምህርት ለትውልድ ኢንሼቲቭ” 372 ሚሊዮን 4መቶ 75 ሺህ በላይ ብር በመሰብሰብ 489 መማሪያ ክፍሎች ግንባታ፤ 1,385 መማሪያ ክፍሎች ጥገና ሥራ ማከናወን ተችሏል። በክልል ደረጃ በልዩ ንቅናቄ 60…

Read More

በከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን ዘርፍ ያሉትን የመልካም አስተዳድር ችግሮችን ለመቅረፍ በቦንጋ ከተማ ውይይት እየተካሄደ ነው።

‎ ‎የ2017 የከተማ ልማት ስራዎች የፈጻሚና አስፈጻሚዎች የአፈጻጸም ሂደት በጥንካሬና በጉድለት በሚያሳይ ግምገማዎች እና በቀጣይ የማስፈጸሚያ አቅጣጫዎች ላይ ውይይት እየተካሄደ ነው። ‎ ‎የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ብልጽግና ፓርቲ ቅ/ጽ/ቤት ኃላፊ ልዩ ረዳት አቶ አለማየሁ አይበራ በመድረኩ እንደገለጹት በብልጽግና ፓርቲ የሚመራ መንግስት ለከተሞች ልማት ከምንጊዜውም በላይ በፖሊሲም ሆነ በተግባር ትኩረት ሰጥቶ እየተገበረ ይገኛል ብለዋል። ‎…

Read More

ለዜጎች የመኖሪያ ቤት ፍላጎት ምላሽ መስጠት የሚያስችሉ ስኬታማ ተግባራት እየተከናወኑ ነው

ለዜጎች የመኖሪያ ቤት ፍላጎት ምላሽ መስጠት የሚያስችሉ ስኬታማ ተግባራት እየተከናወኑ ነው ለዜጎች የመኖሪያ ቤት የፍላጎት ምላሽ ለመስጠት የሚያስችሉ ስኬታማ ተግባራት እየተከናወኑ መሆኑን የከተማና መሰረተ ልማት ሚኒስትር ዴኤታ ሔለን ደበበ ገለጹ። የከተማና መሰረተ ልማት ሚኒስትር ዴኤታ ሔለን ደበበ ለኢዜአ እንደገለጹት፥ የዜጎችን ፈጣን የክትመት ምጣኔ መጨመርን ተከትሎ የመኖሪያ ቤት ፍላጎት በየወቅቱ እያደገ መጥቷል። ቀደም ሲል የቤት አቅርቦት…

Read More

የክልሉ ምክርቤት እያካሄደ ባለው 6ኛ ዙር 4ኛ ዓመት የስራ ዘመን 7ኛ መደበኛ ጉባኤ የተለያዩ ሹመቶችን አጽድቋል ፡፡

ምክር ቤቱ በርዕሰ መስተዳድር ዶክተር ኢንጂነር ነጋሽ ዋጌሾ አቅራቢነት የደቡብ ምዕራብ ሚዲያ ኔትዎርክ የሚመሩ የሥራ አመራር ቦርድ አባላት እንዲሆኑ የቀረቡትን ተቀብሎ በሙሉ ድምጽ አጽድቋል ፡፡ በዚህም መሠረት 1.አቶ ፍቅሬ አማን፣የሥራ አመራር ቦርድ ሰብሳቢ 2.አቶ ነጋ አበራ፣ምክትል ሰብሳቢ 3.አቶ ፋጂዮ ሳፒ ፣አባል 4.አቶ የሺዋስ ዓለሙ፣አባል 5.ወ/ሮ ወሰነች ቶማስ፣አባል 6.አቶ አንድነት አሸናፊ፣አባል 7.አቶ ንጉሴ ወ/ጊዮርጊስ፣አባል ሆነዉ ተሹመዋል፤በምክር…

Read More