በኮንታ እና ካፋ ዞኖች በመሬት መንሸራተት አደጋ ህይወታቸው ላለፉ ዜጎች የክልሉ መንግስት የተሰማውን ልባዊ ሀዘን ይገልጻል ።
የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልላዊ መንግስት ትናንት ምሽቱን የጣለው ከባድ ዝናብ በንብረትና በሰው ህይወት ላይ ጉዳት በማድረሱ ማዘኑን ገልጿል። በኮንታ ዞን አመያ ዙሪያ ወረዳ ጫሬ ዶቄ ቀበሌ ምሽቱን በጣለው ከባድ ዝናብ የ6 ሰዎች ህይወት ሲያልፍ በንብረት ላይ ከፍተኛ ውድመት አስከትሏል። በተመሳሳይ በካፋ ዞን አዲዮ ወረዳ በደረሰዉ የመሬት ናዳ 4 ሰዎች ህይወት አልፏል። በክልላችን አሁንም ከፍተኛ…
