ተረጂነትና ልመናን ለማስቀረት ሁሉ አቀፍ ተግባራት እየተከናወኑ እንደሚገኝ የዞን ዋና አስተዳዳሪዎች ተናገሩ ፡፡
አስተዳዳሪዎቹ ተረጂነትና ልመናን ለማስቀረት ችግሮችን በራስ አቅም የመሸፈን አቅም እየተፈጠረ ይገኛልም ብለዋል ፡፡ ተረጂነትና ልመና እንደ ሀገር መለመድ የለበትም ያሉት የቤንች ሸኮ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ ሀብታሙ ካፍቲን አመራሩ ከህብረተሰቡ ጋር በመወያየት በራስ አቅም ችግሮችን ለመቅረፍ ምርትና ምርታመነትን ለማሳደግ መግባባት ላይ መደረሱን ተናግረዋል ፡፡ በዚህም በሰው ሰራሽና በተፈጥሮ አደጋ የሚከሰተውን ችግር ለመቅረፍ እንዲያስችል በዞኑ ከተለየው…
